Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንዱ ከሌላው ጋር አይጋፋም፤ እያንዳንዱ መስመሩን አይለቅም፤ የጠላትን መሣሪያ ደምስሰው ያልፋሉ፤ ምንም የሚያግዳቸው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መሥመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በጦር መሣርያ መካከል ያልፋሉ፥ የሚያስቆማቸው ነገር የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አንዱ ከሌ​ላው ርቆ አይ​ቆ​ምም፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ይሮ​ጣሉ፤ በመ​ሣ​ሪ​ያ​ቸው ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እነ​ር​ሱም አይ​ጠ​ፉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 2:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕይወታቸውንም ከጥፋት ይጠብቃል፤ ከሞት መቅሠፍትም ይታደጋቸዋል።


ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ።


የአንቺ መተላለፊያ በጣፋጭ ፍሬዎች እንደ ተሞላ እንደ ሮማን የአትክልት ቦታ ነው።


እርሱን ካልሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤ በድንቊርና እንዳሉም ይሞታሉ።


እኔም ሆንኩ የሥራ ጓደኞቼ፥ አገልጋዮቼም ሆኑ የክብር ዘቦቼ፥ ሁላችንም ሌሊት እንኳ ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። በዚህም ዐይነት ውሃ ስንቀዳ እንኳ መሣሪያችን ከእጃችን አልተለየም።


ቅጽሩን የሚሠሩትን ሁሉ ያበረታቱ ነበር፤ ሌላው ቀርቶ፥ ተሸካሚዎቹ ጭምር በአንድ እጃቸው ሲሠሩ፥ በሌላ እጃቸው የጦር መሣሪያ ይዘው ለመከላከል ዝግጁዎች ነበሩ።


ሰይፋቸውን በእጃቸው ያያዙትን ጭፍሮች ሁሉ ንጉሡን ከአደጋ ለመከላከል በመሠዊያው በኩል በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ዙሪያውን ተሰልፈው እንዲቆሙ አደረጋቸው።


በእነርሱ መካከል ደካማና የሚደናቀፍ አይገኝም፤ የሚያንቀላፋና የሚተኛም የለም፤ ትጥቃቸው አይፈታም፤ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።


እንደ ጦረኞች ይጋፈጣሉ፤ እንደ ተዋጊዎችም ቅጽርን ይዘላሉ፤ ሁሉም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይጓዛሉ፤ በማመንታት አቅጣጫቸውን አይለውጡም።


ከተማውን ይወራሉ፤ በከተማውም ቅጽር ላይ ይሮጣሉ፤ እየዘለሉ በቤቶች ላይ ይወጣሉ፤ እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ።


አንበጦች፦ አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ ነገር ግን ሁሉም በሥነ ሥርዓት ይጓዛሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች