Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንደ ጦረኞች ይጋፈጣሉ፤ እንደ ተዋጊዎችም ቅጽርን ይዘላሉ፤ ሁሉም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይጓዛሉ፤ በማመንታት አቅጣጫቸውን አይለውጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤ እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘልላሉ፤ ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣ አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ጦር ሰዎችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፥ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እንደ ተዋ​ጊ​ዎች ይሮ​ጣሉ፤ እንደ ጦረ​ኞ​ችም በቅ​ጥሩ ላይ ይወ​ጣሉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በመ​ን​ገዱ ላይ ይራ​መ​ዳል፤ ከእ​ር​ም​ጃ​ቸ​ውም አያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ሰልፈኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፥ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 2:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንበጦች፦ አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ ነገር ግን ሁሉም በሥነ ሥርዓት ይጓዛሉ።


ከተማውን ይወራሉ፤ በከተማውም ቅጽር ላይ ይሮጣሉ፤ እየዘለሉ በቤቶች ላይ ይወጣሉ፤ እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ።


የሕዝቤን የወይን ተክል ቈራርጠው የሚያበላሹ ጠላቶችን እልካለሁ፤ ነገር ግን ሥር መሠረታቸውን እንዲያጠፉ አላደርግም፤ ቅርንጫፎቹ የእኔ ባለመሆናቸው፥ ቈርጠው እንዲጥሉአቸው አዛለሁ።


በዚያን ቀን ዳዊት አንዲህ አለ፦ “ኢያቡሳውያንን የሚመታ ዳዊት በሚጠላቸው በዕውሮችና በአንካሶች ላይ አደጋ ለመጣል በውሃው መተላለፊያ ይውጣ፤” ስለዚህም ዕውሮችና አንካሶች ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም ተባለ።


“ሳኦልና ዮናታን በአስደናቂ ፍቅር ኖሩ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ላለመለያየት ተባበሩ፤ እነርሱም ከንስር የፈጠኑ፥ ከአንበሳም የበረቱ ነበሩ።


ሙሽራ ከጫጒላ ቤት እንደሚወጣ ፀሐይ ብሩህ ሆኖ ይወጣል፤ ሯጭ በሩጫ ውድድር እንደሚደሰትም ደስ ይለዋል።


እየደጋገመ አቈሰለኝ፤ እንደ ብርቱ ጦረኛም ተንደርድሮ መታኝ።


አንዱ ከሌላው ጋር አይጋፋም፤ እያንዳንዱ መስመሩን አይለቅም፤ የጠላትን መሣሪያ ደምስሰው ያልፋሉ፤ ምንም የሚያግዳቸው የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች