ኤርምያስ 9:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ስለ ተገደሉት ሕዝቤ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፥ ራሴ የውሃ ጒድጓድ፥ ዐይኖቼም የእንባ ምንጭ በሆኑ እንዴት በወደድሁ ነበር! ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጕረፊያ በሆኑልኝ! ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ስለ ተገደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐይኔም የዕንባን ምንጭ ማን በሰጠኝ? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! ምዕራፉን ተመልከት |