Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲሁም የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠበት ዘመንና፥ ከዚያም በኋላ የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ነግሦ ዐሥራ አንድ ዓመት እስከሆነው ድረስ ማለት በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ተወሰደ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል በኤርምያስ አማካይነት ተነግሮአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ንግሠ ዘመን፤ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ ንግሠ ዘመን፤ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት መጨረሻ ድረስ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ሄደበት እስከ ዐምስተኛው ወር ድረስ ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ አሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 1:3
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ።


ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።


“በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”


ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ “ባለፉት ሰባ ዓመቶች በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት እኔን ለማክበር ነበርን?


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ በግዛቱ ሥር ባሉት መንግሥታትና ሕዝቦች ጭምር እየተረዳ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ላይ የጦርነት አደጋ በሚጥልበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።


የኢዮስያስም ልጆች በኲሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛው ኢዮአቄም፥ ሦስተኛው ሴዴቅያስና አራተኛው ሻሉም ናቸው፤


ናቡከደነፆር በኢኮንያን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጐት በይሁዳ አነገሠ፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው።


የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦


የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦


“እኔ እግዚአብሔር አንተን ማናገር ከጀመርኩበት ማለትም ኢዮስያስ ከነገሠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስለ እስራኤል፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብና ስለ ሌሎችም ሕዝቦች ሁሉ የነገርኩህን ቃል ሁሉ በብራና ጻፈው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች