Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 50:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዮሴፍ በአባቱ ሬሳ ላይ ወደቀና ፊቱን እየሳመ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዮሴፍ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ፤ ሳመውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዮሴፍም በአባቱ ፊት ወደቀ፥ በእርሱም ላይ አለቀሰ፥ ሳመውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዮሴ​ፍም በአ​ባቱ ፊት ወደቀ፤ በእ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ሳመ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዮሴፍም በአባቱ ፊት ወደቀ በእርሱም ላይ አለቀሰ፥ ሳመውም

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 50:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በከነዓን ምድር ባለችው “ቂርያት አርባዕ” ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ አዘነ፤ አለቀሰም።


እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እሄዳለሁ፤ ወደዚህ ምድርም ትውልድህን መልሼ አመጣለሁ፤ በምትሞትበትም ጊዜ ዮሴፍ በአጠገብህ ይገኛል።”


ያዕቆብ ለልጆቹ ትእዛዝ መስጠቱን ካበቃ በኋላ፥ እግሮቹን በመኝታው ላይ ሰብሰብ አድርጎ ጋደም እንዳለ በሞት ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ።


ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኃኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት ትእዛዝ ሰጠ።


ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፥ ድምፁን ከፍ በማድረግ “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!” እያለ አለቀሰለት።


አንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ አለቀሱለት።


እናንተም ወላጆች ሆይ! በጌታ በኢየሱስ ሥነ ሥርዓትን በማስተማር፥ በማረምና በመገሠጽ አሳድጉአቸው እንጂ ልጆቻችሁን በማስቈጣት አታስመርሩአቸው።


ወንድሞች ሆይ! ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ስለ ሞቱት ሰዎች እውነቱን እንድታውቁ እንወዳለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች