Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 48:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ያዕቆብ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ልጄ ዮሴፍ እኔ እዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለት ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ናቸው፤ ኤፍሬምና ምናሴ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ይቈጠራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቈጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደ ሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችን ለእኔ ይሁኑ ኤፍሬምን ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤል እንደ ስምዖን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 48:5
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤ እነርሱም ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከኦን ከተማ ካህን ከጶጢፌራ ሴት ልጅ ከአስናት የወለዳቸው ናቸው።


ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።


ከእንግዲህ ወዲህ ሌሎች ልጆች ቢወለዱልህ የአንተ ናቸው፤ ርስት የሚያገኙትም በኤፍሬምና በምናሴ ስም በመጠራት ይሆናል።


አምላክ ሆይ! ውሃው አንተን ባየ ጊዜ ፈራ፤ ጥልቅ ባሕሮችም ተንቀጠቀጡ።


የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።


“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ በርስትነት የምታካፍላቸው የመሬት ድንበር የሚከተለው ነው፤ የዮሴፍ ነገድ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል።


እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ስለ ሆንኩና የእኔ ትሆኑ ዘንድ እናንተን ከአሕዛብ ስለ ለየኋችሁ፥ እናንተ ለእኔ የተቀደሳችሁ ሁኑ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።


ከዮሴፍ ልጆች፦ ከኤፍሬም የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሻማዕ ከምናሴ የጴዳጹር ልጅ ገማልኤል


እኔ አባታችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፥ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።”


እግዚአብሔር በጎ ፈቃዱ ሆኖ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ በፍቅሩ መረጠን።


ያዕቆብ የሚሞትበት ጊዜ ሲቃረብ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና በብትሩ ጫፍ ተደግፎ የሰገደው በእምነት ነው።


ይህንንም ምድር ርስት አድርገህ የምታካፍለው ለዘጠኙ ነገዶችና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ነው።”


የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም በምድሪቱ ለመኖሪያቸው የሚሆኑ ከተሞችና ለከብቶቻቸው ማሰማሪያ የሚሆን መሬት በቀር የርስት ድርሻ አልተሰጣቸውም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች