Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 40:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ፈርዖን በወይን ጠጅ አሳላፊውና በእንጀራ ቤት ኀላፊው እጅግ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በሁለቱም ሹማምቱ ላይ ክፉኛ ተቈጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዥ፥ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ ክፉኛ ተቈጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ፈር​ዖ​ንም በሁ​ለቱ ሹሞች በጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎቹ አለ​ቃና በእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎቹ አለቃ ላይ ተቈጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ፈርዖንም በሁለቱ ሹማምቱ በጠጅ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ አበዛዎቹ አለቃ ላይ ተቆጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 40:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።


ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቈጥቶ ነበር፤ እነርሱም በአንድነት መጡና፤ የንጉሥ ባለሟል ብላስጦስ እንዲተባበራቸው ለምነው እሺ ካሰኙትም በኋላ ንጉሡን ዕርቅ ጠየቁ፤ ይህንንም ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበረ ነው።


ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው።


ግልፍተኛ ሰው ቢኖር የግልፍተኛነቱን ዋጋ እንዲያገኝ ተወው፤ አንድ ጊዜ ከችግሩ ልታወጣው ብትሞክር ሌላ ጊዜም እንዲሁ ማድረግህ አይቀርም።


የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው።


የሰው ቊጣ አንተን ያመሰግንሃል፤ ከጦርነት የተረፉትም በዓልህን ያከብራሉ።


ይህ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን የወይን ጠጅ አሳላፊና የእንጀራ ቤት ኀላፊ ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ።


የወይን ጠጅ አሳላፊውን ወደ ቀድሞ ማዕርጉ መለሰው፤ ስለዚህ የወይን ጠጅ ጽዋውን ለንጉሡ መስጠት ጀመረ።


የወይን ጠጅ አሳላፊው ግን ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ስለ ዮሴፍ የሆነውን ሁሉ ረሳ።


ንጉሥ ሆይ፥ አንተ በእኔና በእንጀራ ቤት ኀላፊው ላይ ተቈጥተህ በዘበኞች አለቃ ቤት እንድንታሰር አድርገህ ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች