Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 38:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ምራቱ እንደ ሆነች ሳያውቅ እርስዋ ወደተቀመጠችበት ወደ መንገድ ዳር ወጣ አለና “እባክሽ ወደ አንች እንድገባ ፍቀጂልኝ” ብሎ ጠየቃት። እርስዋ “ፈቃድህን ብፈጽም ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፣ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፣ “እባክሽ ዐብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፣ “ዐብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፥ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፥ “እባክሽ አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፥ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ እር​ስ​ዋም አዘ​ነ​በለ፥ “እባ​ክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እር​ስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላ​ወ​ቀም ነበ​ርና። እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ ብት​ገባ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ?” አለ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ እርስዋም አዘነበለ፦ እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፦ ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ? አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 38:16
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፊቷን በሻሽ ሸፍና ስለ ነበር ይሁዳ ባያት ጊዜ አመንዝራ ሴት መሰለችው።


እርሱም “ከመንጋዎቼ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርስዋም “እሺ እንግዲያውስ ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ የሚሆን ነገር ስጠኝ” አለችው።


በምታቀርብለትም ጊዜ አፈፍ በማድረግ ይዞ “እኅቴ ሆይ! አብረን እንተኛ!” አላት።


አመንዝራ ሴት ገንዘብ ይከፈላት ነበር፤ አንቺ ግን ገንዘብ በመቀበል ፈንታ ለወዳጆችሽ ስጦታ ታበረክቺአለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋር ያመነዝሩ ዘንድ መደለያ ገንዘብ ሰጠሽ።


“ኢየሱስን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?” አለ። እነርሱም ሠላሳ ጥሬ ብር ሰጡት


እግዚአብሔር ዝሙትን ስለሚጠላ በዚህ ተግባር የተገኘ ገንዘብ የስእለትን መፈጸም የሚያመለክት ስጦታ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር አምላክህ ቤት አይግባ።


ይህም የሚሆነው የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ምንጭ ስለ ሆነ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች