Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 3:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከዔደን የአትክልት ቦታ አስወጣው፤ የተገኘበትንም ምድር እንዲያለማ አደረገው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህ የተገኘበትን ምድር እንዲያርስ፣ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከዔድን የአትክልት ስፍራ አስወጣው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ስለዚህ፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ፥ ጌታ እግዚአብሔር ከዔድን ገነት አስወጣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ስለ​ዚህ የተ​ገ​ኘ​ባ​ትን መሬት ያርስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ደስታ ከሚ​ገ​ኝ​ባት ገነት አስ​ወ​ጣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፤ የተገኘባርን መሬት ያርስ ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 3:23
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዝናብን ባለማዝነቡና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ፥ በምድር ላይ ምንም ዐይነት ተክል አልነበረም፤ ምንም ዐይነት ቡቃያ አልበቀለም።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።


እግዚአብሔር አምላክ በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ቦታን አዘጋጀ፤ የፈጠረውንም ሰው በዚያ እንዲኖር አደረገው።


ወደ መጣህበት ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ፥ እንጀራህን በግንባርህ ላብ ትበላለህ።” ዐፈር ነህና፥ ወደ ዐፈርም ትመለሳለህ።


እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ አዳም ክፉንና ደግን በማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ወስዶ በመብላት ለዘለዓለም እንዲኖር አይገባውም።”


አዳምንም ካስወጣው በኋላ ከዔደን የአትክልት ቦታ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤል የተባሉትን መላእክትንና በየአቅጣጫው እየተገለባበጠ እንደ እሳት የሚንበለበለውን ሰይፍ አኖረ፤ ይህንንም ያደረገው ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይጠጋ ነው።


ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ምንም ፍሬ አትሰጥህም፤ በምድር ላይም ስደተኛ ሆነህ ትንከራተታለህ።”


ቀጥሎም የቃየልን ወንድም አቤልን ወለደች፤ አቤል የበጎች ጠባቂ ሆነ፤ ቃየል ግን ገበሬ ሆነ።


ኖኅ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም መትከል ጀመረ፤


የመሬት ምርት መጨመር ሁሉንም ይጠቅማል፤ ንጉሡ ራሱ ከእርሻው ይጠቀማል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች