Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው ዐደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ “እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 እርሱና ዐብረውት የነበሩ ሰዎችም በልተው፣ ጠጥተው እዚያው ዐደሩ። በማግስቱም ጧት ሲነሡ፣ የአብርሃም አገልጋይ፣ “እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ አሰናብቱኝ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም፥ ከዚያም አደሩ፥ ማልደውም ተነሡና፦ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም ከዚያም አደሩ ማልደውም ተነሡና፦ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:54
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ግን “እባካችሁ አታቈዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብዬ ወደ ጌታዬ ልመለስ” አላቸው።


ስለዚህ ርብቃ ሞግዚትዋን አስከትላ፥ ከአብርሃም አገልጋይና ከእርሱ ሰዎች ጋር እንድትሄድ ፈቀዱላት።


ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድኩበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤


በዚህ ሁኔታ ወንድሞቹን ካሰናበታቸው በኋላ “በመንገድ አትጣሉ” ብሎ መከራቸው።


ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ኢዮአብን “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው የሚገልጠውን መልካም ወሬ ይዤ ወደ ንጉሡ ልሩጥ” አለው።


በሥራው የሠለጠነ ሰው ታያለህን? እንደዚህ ያለ ሰው በተራ ሰው ፊት ሳይሆን በነገሥታት ፊት ለአገልግሎት ይቆማል።


እንዲህ ዐይነቱ ጥያቄ ከብልኅ ሰው የሚመነጭ ስላልሆነ “ከአሁኑ ዘመን ይልቅ በጥንት ዘመን የተደረጉት ነገሮች ሁሉ እንዴት እጅግ የተሻሉ ናቸው?” ብለህ አትጠይቅ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች