Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውንም ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 2:7
33 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ “የመጀመሪያው ሰው አዳም ሕያው ፍጡር ሆነ” ተብሎ ተጽፎአል፤ የኋለኛው አዳም ክርስቶስ ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።


የፈጠረኝ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ሕይወትም የሰጠኝ ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ ነው።


ሥጋ ዐፈር ስለ ሆነ ወደ ዐፈር ይመለሳል፤ ነፍስም ወደ ፈጠራት ወደ እግዚአብሔር ትሄዳለች።


ሆኖም አምላክ ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች ስንሆን አንተ ሠሪአችን ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን።


ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ለሰው ሁሉ የሚሰጥ እርሱ ስለ ሆነ ምንም ነገር አይጐድለውም፤ የሰውም ርዳታ አያስፈልገውም።


የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከመሬት ስለ ሆነ መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው የመጣው ከሰማይ ነው።


ወደ መጣህበት ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ፥ እንጀራህን በግንባርህ ላብ ትበላለህ።” ዐፈር ነህና፥ ወደ ዐፈርም ትመለሳለህ።


እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ሰጥቶኝ እስከ አለሁ ድረስ


በምድር ላይ የሚኖር እስትንፋስ ያለው ነገር ሁሉ ሞተ።


ሰማይን የዘረጋ፥ ምድርን የመሠረተ፥ ለሰውም የሕይወትን እስትንፋስ የሰጠ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል እንዲህ ይላል፦


እግዚአብሔር ከምን እንደ ተፈጠርን ያውቃል፤ ዐፈር መሆናችንንም ያስታውሳል።


እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤ ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን።


አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?


እንግዲህ ትንፋሹ አፍንጫው ላይ በሆነች በሟች ሰው መተማመናችሁ ይቅር፤ እርሱ ለምንም አይጠቅምም።


በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከዔደን የአትክልት ቦታ አስወጣው፤ የተገኘበትንም ምድር እንዲያለማ አደረገው።


ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም!


ሙሴና አሮን በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?”


የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ስለ ሆነ የሰውን ውስጣዊ ሰውነት ሁሉ ይመረምራል።


እነሆ፥ እኔና አንተ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ነን፤ እኔም የተፈጠርኩት ከጭቃ ነው።


ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።


ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።


ይህን ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤


ታዲያ፥ ምስጥ ሳይበላቸው የሚፈርሱ መሠረታቸው ዐፈር በሆነና ከሸክላ በተሠራ ቤት ውስጥ በሚኖሩትማ ላይ እንዴት ይተማመንባቸዋል?


“ለሰው ሁሉ ሕይወትን የምትሰጥ፥ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እረኛ እንደሌለው የበግ መንጋ እንዳይሆን፥ ሕዝብህን የሚመራ አንድ ሰው ምረጥ።”


ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለንግግርም ጊዜ አለው።


በመጀመሪያ የተፈጠረ አዳም ነው፤ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች።


ይሁን እንጂ፥ ከምድር ውስጥ ምንጭ ፈልቆ የብሱን ሁሉ ያጠጣ ነበር።


በሕዝቦች መካከል በእርሱ ጥላ ሥር እንኖራለን ብለን ያሰብነውን እግዚአብሔር የቀባውን የሕይወት እስትንፋሳችን አጠመዱብን።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምላቸውን ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በውስጣችሁ እስትንፋስ በማስገባት እንደገና በሕይወት እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።


በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው።


ጅማትና ሥጋ በመስጠት ቆዳ አለብሳችኋለሁ፤ በውስጣችሁም እስትንፋስ አስገብቼ እንደገና በሕይወት እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።’ ”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች