Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 18:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ መንጋው ሄደና ለግላጋውንና መልካሙን ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም በፍጥነት ዐርዶ አወራርዶ አዘጋጀው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ወደ መንጋው በጥድፊያ ሄዶ፣ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ገር የሆነ ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም ጥጃውን ዐርዶ አዘጋጀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፥ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኰለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰ​ባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጠው፤ ያዘ​ጋ​ጅም ዘንድ ተቻ​ኮለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴንው ስጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 18:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብርሃም ወደ ድንኳኑ ሮጦ ሄደና ሣራን “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውሰጂና አቡክተሽ እንጀራ ጋግሪ” አላት።


አብርሃም እርጎ፥ ወተትና ሥጋ ይዞ ሄደና ምግቡን ለእንግዶቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱ ምግቡን በሚበሉበት ጊዜ አብርሃም ከዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ያስተናግዳቸው ነበር።


ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ።


ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ትተኛላችሁ፤ ከበግ መንጋ የጠቦት ሥጋ፥ ከከብት መንጋ የጥጃ ሥጋ እየበላችሁ በድንክ አልጋ ላይ ታርፋላችሁ!


እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።


“ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንደገና እንዲህ ሲል ላከ፤ ‘ወደ ተጠሩት ሰዎች ሂዱና፦ እነሆ፥ የሠርግ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶአል፤ ስለዚህ ወደ ሠርጉ ግብዣ ኑ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው።


የሰባውን ወይፈን አምጡና ዕረዱ! እንብላ! እንደሰት!


አገልጋዩም ‘ወንድምህ ተመልሶ ስለ መጣ ነው፤ አባትህ በደኅና ስላገኘው የሰባውን ወይፈን ዐርዶለታል’ አለው።


ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’


ሴትዮዋም የሰባ ጥጃ ነበራት እሱንም በፍጥነት ዐረደች፤ ጥቂት ዱቄትም ወስዳ በማቡካት እርሾ ያልነካው ቂጣ ጋገረች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች