Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 17:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፥ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያልሆነ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሕፃ​ኑ​ንም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ትገ​ር​ዙ​ታ​ላ​ችሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለደ ወይም ከዘ​ራ​ችሁ ያይ​ደለ፥ በብ​ርም ከእ​ን​ግዳ ሰው የተ​ገዛ ወንድ ሁሉ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ይገ​ረዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገርዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 17:12
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም በዚያኑ ቀን ልጁን እስማኤልን ገረዘው፤ እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ፥ በቤቱ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፤


ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም ገረዘው።


ባሪያ እንዲሆናችሁ በገንዘባችሁ የገዛችሁት ሰው ግን አስቀድማችሁ ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል።


ከቀንድ ከብቶችህ፥ ከበጎችህም በኲር ሆነው የሚወለዱትን ለእኔ አቅርብ፤ ይኸውም በኲር ሆኖ የተወለደ ወንድ ሁሉ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቈይ፤ በስምንተኛው ቀን ለእኔ ታቀርበዋለህ።


በስምንተኛው ቀን ሕፃኑ መገረዝ አለበት፤


ሕፃኑ በተወለደ በስምንተኛው ቀን፥ በግዝረቱ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ጐረቤቶችዋና ዘመዶችዋ ተሰብስበው መጡ፤ ባባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊጠሩት ፈልገው ነበር፤


ከስምንት ቀን በኋላ ሕፃኑ በሚገረዝበት ሥነ ሥርዓት ላይ፥ ስሙ “ኢየሱስ” ተብሎ ተጠራ። ይህም ገና ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ያወጣለት ስም ነው።


የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።


እንግዲህ በስም ብቻ አይሁዳዊ የሆነ እውነተኛ አይሁዳዊ አይደለም፤ እንዲሁም በውጭ የሚታይ የሥጋ መገረዝ እውነተኛ መገረዝ አይደለም።


እኔ በተወለድኩ በስምንተኛው ቀን ተገርዤአለሁ፤ በትውልዴም ከብንያም ነገድ የሆንኩ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከዚህም የተነሣ ጥርት ያልኩ ዕብራዊ ነኝ። የአይሁድን ሕግ ስለ መጠበቅም ቢሆን ፈሪሳዊ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች