ዘዳግም 22:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እንዲሁም አህያም ሆነ ልብስ ወይም ማንኛውንም ሌላ ነገር ከእስራኤላዊ ወገንህ ጠፍቶ ብታገኝ ችላ ሳትል መልሰህ ስጠው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የወንድምህን አህያ ወይም ልብስ ወይም የጠፋበትን ማንኛውንም ነገር ስታገኝ እንደዚሁ አድርግ፤ በቸልታ አትለፈው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እንደዚሁም ሁሉ በአህያው ወይም በልብሱ ታደርጋለህ፥ ወንድምህ በጠፋው ማንኛውም ነገር ሁሉ ባገኘኸው ጊዜ ታደርጋለህ፥ ቸል ልትለውም አይገባህም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አህያውም ቢሆን፥ በሬውም ቢሆን፥ ወይም ልብሱ ቢሆን እንዲሁ ታደርጋለህ፤ እንዲሁም በወንድምህ በጠፋበት ነገር ሁሉ ባገኘኸው ጊዜ ታደርጋለህ፤ ቸል ልትለው አይገባህም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እንዲህም በአህያው ወይም በልብሱ ታደርጋለህ፤ እንዲህም በወንድምህ በጠፋበት ነገር ሁሉ ባገኘኸው ጊዜ ታደርጋለህ፤ ቸል ልትለው አይገባህም። ምዕራፉን ተመልከት |