Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 7:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ሁለተኛው አውሬ በኋላ እግሮቹ ሸብረክ ብሎ እንደ ቆመ ድብ ይመስል ነበር፤ በጥርሶቹም ሦስት የጐድን አጥንት ነክሶ ይዞአል፤ ‘የፈለግኸውን ያኽል ሥጋ ብላ!’ የሚል ድምፅም ተነገረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “እነሆም፤ ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጐኑ ከፍ ብሏል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጐድን ዐጥንቶች ነበሩት። እርሱም፤ ‘ተነሥ፤ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ!’ ተባለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፥ እንደዚህም፦ ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ ተባለላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 7:5
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአንተ በኋላ በገናናነቱ የአንተን መንግሥት የሚያኽል አነስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዓለምን ሁሉ የሚገዛ በነሐስ የሚመሰል መንግሥት በሦስተኛ ደረጃ ይነሣል።


ግልገሎችዋ የተወሰዱባት ድብ እንደምታደርግ እኔም አደጋ እጥልባችኋለሁ፤ እቦጫጭቃችሁማለሁ፤ እንደሚባላ አንበሳ እሆንባችኋለሁ፤ እንደሚበጣጥስ ክፉ አውሬም እበጣጥሳችኋለሁ።


እኔም አሁን የምነግርህ ነገር እውነት ነው።” ያም ሰው የሚመስለው መልአክ እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፦ “ሌሎች ሦስት ነገሥታት በፋርስ ላይ ይነግሣሉ፤ ከእነርሱ የሚከተለው አራተኛው ንጉሥ ከሌሎቹ ይልቅ በሀብት የከበረ ይሆናል፥ ከሀብቱም የተነሣ ኀይሉ በበረታ ጊዜ ሌሎቹን መንግሥታት በማስተባበር በግሪክ መንግሥት ላይ ይነሣል።


ፋርስ ‘መንግሥትህ ተከፍሎ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ’ ማለት ነው።”


የባዕድ አገር ሕዝቦች እንደ አራዊት እየፈነጩ መጥተው ሕዝቡን ይውጡ ዘንድ እግዚአብሔር አዞአቸዋል፤ እርሱም እንዲህ ይላል፦


ሞኝን የሞኝነት ሥራ ሲሠራ ከመገናኘት ይልቅ ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል።


ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።


ያየሁት አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፥ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው።


የመጀመሪያው አውሬ አንበሳ ይመስል ነበር፤ እርሱም እንደ ንስር ያሉ ክንፎች ነበሩት፤ እኔም እየተመለከትኩት ክንፎቹ ተነቃቀሉ፤ አውሬውም ቀና ብሎ እንደ ሰው በሁለት እግሮቹ ቆመ፤ ሰብአዊ አእምሮም ተሰጠው።


“ይህንን በመመልከት ላይ ሳለሁ እነሆ፥ ሌላ ነብር የሚመስል አውሬ ወጣ፤ እርሱም የወፍ ክንፎች የሚመስሉ አራት ክንፎች በጀርባው ላይ ነበሩት፤ አራት ራሶችም ነበሩት፤ የገዢነት ሥልጣንም ተሰጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች