Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጥበበኞቹም ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ነገር ግን ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጒሙን ለንጉሡ ማስረዳት የቻለ ከእነርሱ መካከል የተገኘ ማንም አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ነገር ግን ጽሕፈቱን ሊያነብብም ሆነ ትርጕሙ ምን እንደ ሆነ ለንጉሡ ሊነግር የሚችል ማንም አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የዚያን ጊዜም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፥ ነገር ግን ጽሕፈቱን ያነብቡ፥ ፍቺውንም ለንጉሡ ያስታወቁ ዘንድ አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 5:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! አንተ የጠየቅኸውን ምሥጢር ጠቢባንም ሆኑ አስማተኞች፤ ጠንቋዮችም ሆኑ መተተኞች ሊነግሩህ አይችሉም።


ጠንቋዮች፥ አስማተኞች፥ ኮከብ ቈጣሪዎችና መተተኞች ሁሉ ወደ እኔ በመጡ ጊዜ ሕልሜን ነገርኳቸው፤ እነርሱ ግን የሕልሜን ትርጒም ሊነግሩኝ አልቻሉም፤


ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።


እነሆ፥ ጠቢባን አማካሪዎቼና አስማተኞች ሁሉ ይህን ጽሕፈት አንብበው እንዲተረጒሙልኝ ተጠርተው ወደ እኔ መጥተው ነበር፤ ነገር ግን ተርጒመው ሊያስረዱኝ አልቻሉም፤


እነዚህ ሁለቱም ነገሮች በቅጽበት በአንድ ቀን በአንቺ ላይ ይደርሳሉ፤ ምንም ያኽል መተትሽ ትልቅ፥ ጥንቈላሽም ብዙ ቢሆን የልጆችና የባል ሞት በአንቺ ላይ በሙላት ይደርሳል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በባቢሎን፥ በሕዝቦችዋ፥ በመሪዎችዋና በጥበበኞችዋ ላይ ሰይፍ ይመዘዝ!


“እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።”


“እኔ ናቡከደነፆር በቤተ መንግሥቴ በብልጽግናና በምቾት እኖር ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች