ዳንኤል 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዝ በላይ በኩል የቆመው መልአክ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ በዘለዓለማዊው አምላክ ስም በመማል “ሦስት ዓመት ተኩል ይወስዳል፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሚደርሰው መከራ ሲያከትም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተፈጻሚነት ያገኛሉ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመንም እኩሌታ ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኀይል መሰበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላለም በሚኖረው በርሱ ሲምል ሰማሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፦ ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው፥ የተቀደሰውም ሕዝብ ኃይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል ብሎ ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ። ምዕራፉን ተመልከት |