Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ጢሞቴዎስ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የኢያኔስና የኢያንበሬስ ሞኝነት እንደ ተገለጠ የእነዚህም ሰዎች ሞኝነት በሰው ሁሉ ፊት ስለሚገለጥ አይሳካላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይሁን እንጂ አይሳካላቸውም፤ ምክንያቱም የእነዚያ ሰዎች ሞኝነት እንደ ተገለጠ ሁሉ፣ የእነዚህም ለሁሉ ግልጽ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዳሩ ግን እነዚያ ሁለቱ ተቃዋሚዎች እንደሆኑት እንዲሁ የእነዚህም ሰዎች ሞኝነት ለሁሉም ሰው ስለሚገለጥ አይሳካላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ጢሞቴዎስ 3:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚክያስም “በስተ ጓሮ በኩል ወዳለው ክፍል ሄደህ በምትሸሸግበት ጊዜ ታገኘዋለህ” ሲል መለሰለት።


የሰው ቊጣ አንተን ያመሰግንሃል፤ ከጦርነት የተረፉትም በዓልህን ያከብራሉ።


ከዚህም በኋላ ፈርዖን ጠቢባኑንና አስማተኞቹን ጠራ፤ እነርሱም በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ።


በትሮቻቸውን ወደ መሬት በጣሉአቸው ጊዜ ተለውጠው እባቦች ሆኑ፤ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን በትሮች ሁሉ ዋጠች።


እንደማንኛውም ግብጻዊ እነርሱም ቈስለው ስለ ነበረ በዚያን ጊዜ አስማተኞቹ በሙሴ ፊት መቅረብ አልቻሉም፤


ለመሆኑ ‘የባቢሎን ንጉሥ በአንተም ሆነ በአገርህ ላይ አደጋ አይጥልም’ ብለው የነገሩህ ነቢያትህ አሁን የት አሉ?


የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን በጣም ተቈጥተው በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተመካከሩ።


አሁንም እነሆ፥ የጌታ እጅ ይመታሃል፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ ለጥቂት ጊዜም የፀሐይን ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑ ዐይኖቹን ጭጋግና ጨለማ ሸፈናቸው፤ እጁን ይዞ የሚመራውንም ሰው ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ።


ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደ ተቃወሙት እነዚህ ሰዎች አእምሮአቸው የተበላሸና በእምነትም ነገር ውድቀት የደረሰባቸው ስለ ሆነ እውነትን ይቃወማሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች