Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 7:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ይህም በዐይንህ ፊት ያነሰ ሆኖ አሁንም የበለጠ ነገር እያደረግህ ነው፤ ስለ ባሪያህ ልጆች ለሚመጡት ዘመናት ብዙ የተስፋ ቃል ተናግረሃል፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ይህ ለሰው ሁሉ የተለመደ ድርጊትህ ነውን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ በፊትህ ጥቂት ሆኖ ሳለ አንተ ግን ስለ ወደ ፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገርህ፤ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰው ጋራ የምታደርገው ግንኙነት ለካ እንዲህ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ በፊትህ ጥቂት ሆኖ ሳለ፤ አንተ ግን ስለ ወደ ፊቱ የአገልጋይህ ቤት ተናገርህ፤ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰው ጋር የምታደርገው ግንኙነት ለካ እንዲህ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እኔ በፊ​ትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪ​ያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፥ ስለ ባሪያህም ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፥ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 7:19
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መንግሥቱንና ሚስቶቹን ሰጠሁህ፤ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ አነገሥኩህ፤ ይህም ሁሉ እንኳ የማይበቃህ ቢሆን ኖሮ በተጨማሪ እጥፍ አድርጌ በሰጠሁህ ነበር፤


ነገር ግን ይህን ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀላል ነገር ነው፤ ከዚህም በላይ እርሱ በሞአባውያን ላይ ድልን ያጐናጽፋችኋል።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ያለፈው ሁሉ በፊትህ የማይበቃ ሆኖ ስለ አገልጋይህ ቤት ለሚመጣው ሩቅ ዘመን አሁንም እንደገና እኔን እንደ ትልቅ ባለማዕርግ አድርገህ ተመለከትከኝ።


አምላክ ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው! ሰዎች በአንተ ጥበቃ ሥር ይከለላሉ።


ከመልካሙ መሰማሪያ የተመገባችሁት አንሶ ነውን? የቀረውን መሰማሪያችሁን በእግራችሁ የምትረግጡት? የጠራ ውሃ ከጠጣችሁ በኋላ የቀረውን ማደፍረስ አለባችሁን?


“በምድረ በዳ እንድንሞት በማርና በወተት ከበለጸገችው ምድር ያስወጣኸን አንሶ አሁን ደግሞ በእኛ ላይ አለቃ ልትሆን ትፈልጋለህን?


ወደ እርሱ ቀርባችሁ በማደሪያው ድንኳን አገልግሎታችሁን እንድትፈጽሙና በፊታቸውም ቆማችሁ የእስራኤልን ጉባኤ እንድታገለግሉ የእስራኤል አምላክ ከሌላው የእስራኤል ማኅበር መካከል መርጦ እናንተ የተለያችሁ እንድትሆኑ ማድረጉን እንደ ቀላል ነገር ታዩታላችሁን?


ይህንንም ያደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የገለጠውን ቸርነትና ወደር የሌለውን የጸጋውን ብልጽግና በሚመጡት ዘመናት ሊያሳየን ብሎ ነው።


ጐልማሳውም “የእናንተም ሆነ የጠላት ወገን አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥ እንደ መሆኔ መጠን እነሆ፥ መጥቻለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ መሬት ወድቆ ሰገደለትና “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ ምን ልታዘዝ?” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች