Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መገደሉን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በድንጋጤ ተሸበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አበኔር በኬብሮን መሞቱን የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በሰማ ጊዜ ወኔ ከዳው፤ መላው እስራኤልም ደነገጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መሞቱን በሰማ ጊዜ ወኔ ከዳው፤ መላው እስራኤልም ተሸበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የሳ​ኦ​ልም ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ አበ​ኔር በኬ​ብ​ሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆ​ቹም ደከሙ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ሁሉ ደነ​ገጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የሳኦልም ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ እጁ ደከመች፥ እስራኤላውያንም ሁሉ ደነገጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 4:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤


የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ ጋር የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ማሕናይም ሸሽቶ ሄደ፤


አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።


ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ነዋሪዎች የሆኑት ሕዝቦች አይሁድን በማስፈራራትና ተስፋ ለማስቈረጥ በመሞከር ቤተ መቅደሱን እንዳይሠሩ ሊከለክሉአቸው ተነሣሡ።


በዚህም ዐይነት ሥራውን እንድናቆም ለማድረግ ያስፈራሩን ነበር፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እባክህ አበርታኝ!” ስል ጸለይኩ።


ከፍርሃት የተነሣ የእያንዳንዱ ሰው እጅ ይዝላል፤ የእያንዳንዱም ሰው ልብ በፍርሃት ይዋጣል፥


የደከሙትን ክንዶች አጠንክሩ፥ የተብረከረኩ ጒልበቶችንም አጽኑ።


የባቢሎን ንጉሥ ይህን ወሬ ሲሰማ እጁ ሽባ ሆኖ ተንጠልጥሎ ይቀራል፤ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ይጨነቃል።


የኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ወሬውን ስለ ሰማን ክንዳችን ዛለ፤ በምጥ እንደ ተያዘች ሴትም ጭንቀትና ሕመም ተሰምቶናል፤


በዚያን ጊዜ ስለ ኢየሩሳሌም እንደዚህ ይባልላታል፤ “የጽዮን ከተማ ሆይ! አትፍሪ! ክንዶችሽም አይዛሉ!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች