Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 24:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢዮአብም በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፥ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ በውትድርና ለማገልገል ብቃት ያላቸው ሰዎች መኖራቸውንም ለንጉሡ አሳወቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢዮአብም የሕዝቡን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፥ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢዮ​አ​ብም የሕ​ዝ​ቡን ቍጥር ድምር ለን​ጉሡ ሰጠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይ​ሁ​ዳም ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎች አም​ስት መቶ ሺህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፥ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፥ የይሁዳም ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 24:9
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህ ዐይነት በመላ ሀገሪቱ ሲዘዋወሩ ቈይተው ዘጠኝ ወር ከኻያ ቀን ከሆናቸው በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


ከይሁዳ ነገድ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው፥ እንደየስማቸው ቊጥር፥ ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ከይሁዳ ነገድ የተቈጠሩት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች