Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 23:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱን ለመዳሰስ የብረት ልብስ ወይም የጦር ዛቢያ ያስፈልጋል፤ በዚያን ጊዜ ባሉበት ፈጽመው ይቃጠላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣ የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እሾኽ የሚነካ ሁሉ፥ የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ እነሱም ባሉበት ስፍራ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠ​ሉና በው​ር​ደ​ታ​ቸው ከሚ​ነ​ድዱ በቀር በብ​ረት ብዛ​ትም ሆነ፥ በጦር ዘንግ ብዛት ሰው የሚ​ደ​ክ​ም​ባ​ቸው አይ​ደ​ሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ማናቸውም ሰው ይነካው ዘንድ ቢወደድ፥ በእጁ ብረትና የጦሩን የቦ ይይዛል፥ በሥራቸውም በእሳት ፈጽሞ ይቃጠላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 23:7
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ፤ ዘራቸውንም ከሕዝቦች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ።


ዳግመኛ በወይን ቦታዬ ላይ አልቈጣም፤ የወይን ቦታዬን የሚያበላሹ ኲርንችትና እሾኽ ቢኖሩ ነቃቅዬ በእሳት በማቃጠል ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ።


እናንተ ለኖራ እንደሚቃጠሉና ለእሳት እንደሚቈረጥ እሾኽ ትሆናላችሁ።


“ነገር ግን የሰው ልጅ ሆይ! እነርሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ፤ እንደ እሾኽና እንደ አሜከላ ሆነውብህ በጊንጦች መካከል እንደምትኖር ሆነህ ቢሰማህም ቃላቸውንም ሆነ የእነዚያን ዐመፀኞች የቊጣ ፊት ከቶ አትፍራ።


ስለዚህ ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጐተራዬ ክተቱ’ እላቸዋለሁ።”


ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለ ነበር፥ ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም ሲሉ እርሱ ከሄደ በኋላ መልእክተኛ ላኩ።


በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው።


በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።


ከሰማይ የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀጣቸዋል።


ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያጠፋውና በግርማ መምጣቱ የሚደመስሰው የዐመፅ ሰው ይገለጣል።


እሾኽና አሜከላ ብታበቅል ግን ዋጋቢስ ትሆናለች፤ በቅርብ ጊዜም ትረገማለች፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች