Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በጣም በርትተውብኝ ከነበሩት ከኀይለኞች ጠላቶቼና ከሚጠሉኝ ሰዎች ሁሉ እጅ እግዚአብሔር አዳነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በርትተውብኝ ነበርና፥ ከብርቱ ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም ታደገኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከብ​ር​ቱ​ዎች ጠላ​ቶቼ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ኝም አዳ​ነኝ፤ በር​ት​ተ​ው​ብኝ ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:18
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


ስለዚህ እርሱ ለሞት ከሚያደርስ አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ደግሞም እንደሚያድነን ተስፋችን በእርሱ ነው።


እኔ ወደ አንተ በምጣራበት ቀን፥ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንም በዚህ ዐውቃለሁ።


ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ።


እግዚአብሔር ዳዊትን ከሳኦልና ከሌሎቹም ጠላቶቹ እጅ በመታደግ ባዳነው ጊዜ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ክብር ዘመረ፦


እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ።


እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ።


ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤ ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥ ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ እንደ አንተ ያለ ማነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች