Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 2:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 አበኔርና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ በመጓዝ በዓራባ ሸለቆ በኩል ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግረው በመጓዝ ቢትሮንን ሁሉ ዓልፈው ወደ ማኅናይም መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ዓረባን ዐልፈው ሄዱ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን በመሻገር ቢትሮንን ሁሉ ዐልፈው ወደ መሃናይም መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ዓራባን አልፈው ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም በመሻገር ቢትሮንን ሁሉ ዐልፈው ወደ ማሕናይም መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 አበ​ኔ​ርና ሰዎ​ቹም ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ ምዕ​ራብ ሄዱ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ ያን ቀጥ​ተኛ መን​ገድ ካለፉ በኋ​ላም ወደ ሰፈር መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ዓረባ እያለፉ ሄዱ፥ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ ቢትሮንንም ሁሉ ካለፉ በኋላ ወደ መሃናይም መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 2:29
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮአብ አበኔርን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በዚህ ጊዜ ከዳዊት ሰዎች መካከል ከዐሣሔል ሌላ ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች መጒደላቸው ታወቀ።


የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ ጋር የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ማሕናይም ሸሽቶ ሄደ፤


ከገቡም በኋላ ወደ ኢያቡስቴ መኝታ ክፍል ዘለቁ፤ እርሱም በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ወግተው ገደሉት፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱ፤ ሌሊቱንም ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ በኩል አልፈው ሄዱ፤


የሌሊቱ ጨለማ እስከሚወገድ፤ የማለዳው ነፋስ እስከሚነፍስ፤ ውዴ ሆይ! እንደ ዋልያ ወይም እንደ አጋዘን ግልገል በገደላማ ተራራዎች ላይ እየሮጥክ ተመለስ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች