Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ባርዚላይ ሰማኒያ ዓመት የሞላው ሽማግሌ ሰው ነበር፤ በጣም ሀብታም ከመሆኑም የተነሣ ንጉሥ ዳዊት በማሕናይም በነበረበት ጊዜ ይኸው ባርዚላይ ምግብ ያቀርብለት ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በዚያ ጊዜ ቤርዜሊ በዕድሜ የገፋ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ እጅግ ባለጠጋ ስለ ነበረም ንጉሡ በመሃናይም ሳለ የሚመገበውን አምጥቶለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እንዲሁም ገለዓዳዊው ባርዚላይ ከሮገሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም አብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ቤር​ዜ​ሊም እጅግ ያረጀ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ እጅ​ግም ትልቅ ሰው ነበ​ረና ንጉሡ በመ​ና​ሄም ሳለ ይቀ​ል​በው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ቤርዜሊም እጅግ ያረጀ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበረ፥ እጅግም ትልቅ ሰው ነበረና ንጉሡ በመሃናይም ሳለ ይቀልበው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:32
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያም ቤተሰቡ ከካሌብ ጐሣ የሆነ ናባል ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የማዖን ተወላጅ ሲሆን በቀርሜሎስ ከተማ አጠገብ የእርሻ መሬት ነበረው፤ ታላቅ ባለጸጋ ከመሆኑም የተነሣ ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ ሚስቱ አቢጌልም እጅግ የተዋበች አስተዋይ ሴት ስትሆን እርሱ ግን መልካም ጠባይ የጐደለው ባለጌ ሰው ነበር። ናባል በቀርሜሎስ በጎቹን ያሸልት ነበር፤


ሽበት የክብር ዘውድ ነው። የሚገኘውም በተቀደሰ አኗኗር ነው።


በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ኻያ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን ዐይኑ ያልፈዘዘና ጒልበቱም ያልደከመ ገና ብርቱ ሰው ነበር።


ያዕቆብ ዐሥራ ሰባት ዓመት በግብጽ አገር ኖረ፤ ዕድሜውም መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆኖት ነበር።


የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤


ዕድሜውም 950 ዓመት ሲሆነው ሞተ።


ዕድሜው 969 ሲሆነውም ሞተ።


ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፤ አስከሬኑንም በሽቶ አሽተው በማድረቅ በግብጽ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።


ንጉሡም ባርዚላይ “ከእኔ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ና፤ እኔም በተድላና በደስታ እንድትኖር አደርግሃለሁ” አለው።


ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ።


ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንዲሁ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች