Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ሺምዒንም “በሞት እንደማትቀጣ ቃል እገባልሃለሁ!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህ ንጉሡ ሳሚን፣ “አትሞትም” አለው፤ ይህንም ንጉሡ በመሐላ አጸናለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ዳዊትም፥ “እናንት የጽሩያ ልጆች፥ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ ስለምን ጠላቶች ትሆኑብኛላችሁ? ዛሬ ማንስ ቢሆን በእስራኤል ዘንድ መሞት አለበት? እኔ በእስራኤል ላይ ንጉሥ መሆኔን ያወቅሁበት ቀን አይደለምን?” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ንጉ​ሡም ሳሚን፥ “አት​ሞ​ትም” አለው። ንጉ​ሡም ማለ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ንጉሡም ሳሚን፦ አትሞትም አለው። ንጉሡም ማለለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:23
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዐይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።


ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂ ራስህ ነህ።”


ሰዎች ሲምሉ ከራሳቸው በሚበልጥ ስም ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት በመካከላቸው ያለውን ክርክር ሁሉ ያስወግዳሉ።


ዳዊትም “እነዚያ ወራሪዎች ወዳሉበት ስፍራ ልትመራን ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እንደማትገድለኝና ለጌታዬም አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ ከማልክልኝ ላሳይህ እችላለሁ” ሲል መለሰለት።


ከዚያም በኋላ ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዐይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” አላት።


ከዚህ በኋላ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት ንጉሡን ለመቀበል ወረደ፤ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን በድል አድራጊነት እስከ ተመለሰበት ጊዜ ድረስ መፊቦሼት እግሩን አልታጠበም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም።


ሳኦል ግን “በዛሬው ቀን እግዚአብሔር እስራኤልን ስላዳነ ማንም ሰው መገደል የለበትም” አለ።


ንጉሡም አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህ እናንተን አይመለከታችሁም፤ እግዚአብሔር አዞት ቢረግመኝ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ለመጠየቅ መብት የሚኖረው ማን ነው?” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች