Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 17:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ነገር ግን አንድ ቀን አንድ ልጅ እነርሱን ስላያቸው ሄዶ ለአቤሴሎም ነገረው፤ ስለዚህ እነርሱ በባሑሪም በሚገኘው በአንድ ሰው ቤት ለመሸሸግ ሮጠው ሄዱ፤ ሰውየው በቤቱ አጠገብ የውሃ ጒድጓድ ስለ ነበረው ወደዚያ ውስጥ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሆኖም አንድ ወጣት አያቸውና ለአቤሴሎም ነገረው፤ ስለዚህ ሁለቱም በፍጥነት ተነሥተው በባሑሪም ወደሚገኝ ወደ አንድ ሰው ቤት ሄዱ፤ ሰውየው በግቢው ውስጥ ጕድጓድ ስለ ነበረው ወደዚያው ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሆኖም አንድ ወጣት አይቷቸው ለአቤሴሎም ነገረው፤ ሁለቱም በፍጥነት ተነሥተው በባሑሪም በግቢው ውስጥ ጉድጓድ ወደሚገኝ ወደ አንድ ሰው ቤት ሄዱ፤ ወደዚያም ውስጥ ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አንድ ብላ​ቴ​ናም አይቶ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ነገ​ረው፤ እነ​ርሱ ግን ፈጥ​ነው ሄዱ፤ ወደ ባው​ሪ​ምም ወደ አንድ ሰው ቤት መጡ፤ በግ​ቢ​ውም ውስጥ ጕድ​ጓድ ነበ​ረው፤ ወደ​ዚ​ያም ውስጥ ወረዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አንድ ብላቴናም አይቶ ለአቤሴሎም ነገረው፥ እነርሱ ግን ፈጥነው ሄዱ፥ ወደ ብራቂምም ወደ አንድ ሰው ቤት መጡ፥ በግቢውም ውስጥ ጉድጓድ ነበረ፥ ወደዚያም ውስጥ ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 17:18
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም በደረሰ ጊዜ ከሳኦል ዘመዶች አንዱ የሆነው የጌራ ልጅ ሺምዒ ሊገናኘው ወጥቶ እየተራገመ ወደ እርሱ ቀረበ፤


በዚያኑ ጊዜም የባሑሪም ተወላጅ የሆነው የጌራ ልጅ ብንያማዊው ሺምዒ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ፈጥኖ ሄደ፤


ባልዋ ፓልጢኤልም እያለቀሰ እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ ተከተላት፤ ነገር ግን አበኔር “ወደ ቤትህ ተመለስ” ባለው ጊዜ ተመለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች