Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 17:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ እርሱና አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤላውያን መሪዎች የሰጡትን ምክር ሑሻይ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ነገራቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኩሲም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፤ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሯቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሑሻይ ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፥ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች እንዲህ እንዲህ አድርጉ ሲል መክሮአቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አር​ካ​ዊው ኩሲም ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር፥ “አኪ​ጦ​ፌል ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲ​ህና እን​ዲህ መክ​ሮ​አል፤ እኔ ግን እን​ዲ​ህና እን​ዲያ መክ​ሬ​አ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፦ አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፥ እኔ ግን እንዲህና እንዲህ መክሬአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 17:15
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም ከሄዱ በኋላ አሒማዓጽና ዮናታን በፍጥነት ከጒድጓዱ ወጥተው በመሄድ የሆነውን ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩት፤ አኪጦፌል በእነርሱ ላይ ዐቅዶት የነበረውን ካስረዱት በኋላም “ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር!” አሉት።


የአሒጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቤሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሠራያ ደግሞ ጸሐፊ ነበረ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች