Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 14:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የራሱ ጠጒር እጅግ ብዙ ነበር፤ ስለሚረዝምበትና ስለሚከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቈርጠው ነበር፤ የጠጒሩም ክብደት በቤተ መንግሥት ሚዛን ሲለካ ከሁለት ኪሎ በላይ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የራስ ጠጕሩ ሲከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቈርጠው ነበር፤ የተቈረጠውን በሚመዝነው ጊዜ ክብደቱ በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ይሆን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የራስ ጠጉሩ ሲከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቆርጠው ነበር፤ የተቆረጠውን በሚመዝነው ጊዜ ክብደቱ በቤተ መንግሥት ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ይሆን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ቀድሞ በመ​ጀ​መ​ሪያ ዘመን ጠጕሩ ይከ​ብ​ደው ነበ​ርና በዓ​መት አንድ ጊዜ ይቈ​ረ​ጠው ነበር፤ ሲቈ​ረ​ጥም የራሱ ጠጕር በን​ጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመ​ዝን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ጠጕሩም ይከብደው ነበርና በዓመት አንድ ጊዜ ይቆርጠው ነበር፥ ሲቆርጥም የራሱ ጠጕር በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመዘን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 14:26
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ካህናቱ ራሳቸውን መላጨትም ሆነ ጠጒራቸውን ማሳደግ አይገባቸውም፤ ነገር ግን ፀጒራቸውን በሚገባ ሁኔታ ያስተካክሉ።


ወንድ ጠጒሩን ቢያስረዝም ነውር እንደሚሆንበት ተፈጥሮ ራሱ ያስተምራችሁ የለምን?


በድንገት፥ አቤሴሎም ከዳዊት ተከታዮች ጥቂቱን አገኘ፤ አቤሴሎም በዚያን ጊዜ በበቅሎ ላይ ተቀምጦ ይጋልብ ስለ ነበር በቅሎዋ በአንድ ትልቅ የወርካ ዛፍ ሥር ስታልፍ ሳለ የዛፉ ቅርንጫፍ የአቤሴሎምን ራስ ጠጒር ያዘበት፤ በቅሎዋም በእግሮቹ መኻል ሾልካ ስትሄድ አቤሴሎም በዐየር ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ።


ስለዚህ በሽቶ ፈንታ ግማት፥ በጥሩ መታጠቂያ ፈንታ ገመድ፥ በጐፈሬ ፈንታ ቡሃነት፥ በመጐናጸፊያ ፈንታ ማቅ፥ በውበትም ፈንታ ጠባሳ መሆን ይመጣባቸዋል!


ትክክለኞች የሆኑ ሚዛኖች ማለት የርዝመት፥ የክብደትና የፈሳሽ መለኪያዎች ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


አብርሃምም በነገሩ ተስማምቶ ዔፍሮን በሕዝቡ ፊት በተናገረው መሠረት በነጋዴዎች ሚዛን ልክ አራት መቶ ብር መዝኖ ሰጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች