Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፥ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም፥ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:28
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ሁለቱ ሰዎች ተቀምጠው አብረው ተመገቡ፤ የሴቲቱም አባት ሌዋዊውን “እባክህ ዛሬ ደስ ብሎህ እዚሁ ዕደር” አለው።


እየተደሰቱ ሳለም ከከተማይቱ የመጡ ጋጠወጦች በድንገት ቤቱን ከበው በሩን መደብደብ ጀመሩ፤ ሽማግሌውንም “ያንን ወደ ቤትህ የገባውን ሰው ግብረ ሰዶም እንድንፈጽምበት አውጣልን!” አሉት።


ሌዋዊውና ቊባቱ እንዲሁም አገልጋዩ ሆነው እንደገና ጒዞ ሲጀምሩ የልጅቱ አባት እንዲህ አለ፤ “ተመልከቱ! እነሆ ጊዜው መሽቶአል፤ ሌሊቱን እዚሁ ብታሳልፉ ይሻላል፤ አሁን ፈጥኖ ይጨልማል፤ እዚሁ ደስ ብሎአችሁ ዕደሩ፤ ነገ በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞ በመጀመር ወደ ቤታችሁ ትሄዳላችሁ።”


ቦዔዝ ከበላና ከጠጣ በኋላ ደስ ብሎት ነበር፤ ወደ ገብሱም ክምር ሄዶ ጋደም አለና አንቀላፋ፤ ሩትም በቀስታ ወደ እርሱ ተጠጋች፤ ልብሱንም ገለጥ አድርጋ በእግሩ አጠገብ ተኛች።


ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያት ግን እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ለሰው ከመታዘዝ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባናል፤


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።


እናንተ ሰካራሞች! እርስ በርሱ የተያያዘ እሾኽና ድርቆሽ በእሳት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ፥ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


በዚያኑ ሌሊት የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ፤


በምግብና በወይን ጠጅ ተድላ ደስታ ይገኛል፤ ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ያለ ገንዘብ አይገኝም።


እግዚአብሔር ቀድሞ የፈቀደልህ ይህ በመሆኑ ሂድ፤ ምግብህን ተመግበህ፥ የወይን ጠጅህንም ጠጥተህ በመርካትህ ደስ ይበልህ።


ስለዚህ ልቡን ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፥ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና ብርታት የሚሰጠውን ምግብ ያዘጋጃል።


ግብዣው በተጀመረ በሰባተኛው ቀን ንጉሥ አርጤክስስ በወይን ጠጅ ረክቶ ደስ ባለው ጊዜ መሁማን፥ ቢዝታ፥ ሐርቦና፥ ቢግታ፥ አባግታ፥ ዜታርና ካርካስ ተብለው የሚጠሩትን ጃንደረቦች የሆኑትን ሰባቱን የእልፍኝ አገልጋዮቹን ወደ እርሱ ጠርቶ፥


ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች የሆኑ ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ በመጠጥ ሰክረው በነበሩበት ጊዜ እኩለ ቀን ላይ የእስራኤል ሠራዊት ወጣ፤


የጻፈውም ቃል “ኦርዮን ጦርነቱ በተፋፋመበት ግንባር አሰልፈው፤ ከዚያም አንተ ወደ ኋላ አፈግፍገህ እርሱ እንዲገደል አድርገው” የሚል ነበር።


ዳዊትም ኦርዮን ራት ጋበዘውና እስኪሰክር ድረስ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ አደረገው፤ በዚያም ሌሊት ኦርዮ በቤተ መንግሥቱ ዘበኞች ቤት ብርድ ልብሱን በማንጠፍ ተኝቶ ዐደረ እንጂ ወደ ቤቱ አልሄደም።


ንጉሡም “አይዞሽ አትፍሪ! ይልቅስ የምታዪው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እኔ አንድ መለኮታዊ ግርማ ያለው ከመቃብር ሲወጣ እያየሁ ነኝ” አለችው።


ከዚያም በኋላ ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዐይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” አላት።


በምትሄድበት ሁሉ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለምሆን አይዞህ! በርታ! አትፍራ! ብዬ አዝሃለሁ።”


ከዕለታት አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ ልብሱንም አውልቆ ራቊቱን በድንኳን ውስጥ ተኛ።


አንተ ለእኔ ስላልታዘዝክ የኦርዮን ሚስት ስለ ወሰድክ፥ እነሆ ከቤትህ በሰይፍ የሚገደል አይጠፋም፤


አቤሴሎም አጥብቆ ስለ ጠየቀ ዳዊት፥ አምኖንና የቀሩትም ወንዶች ልጆቹ ሁሉ እንዲሄዱ ፈቀደ። አቤሴሎም ለንጉሥ የሚገባ ግብዣ አዘጋጅቶ ነበር፤


ከዚህ በኋላ የግብጽ ንጉሥ አዋላጆቹን አስጠርቶ “ወንዶች ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ያደረጋችኹበት ምክንያት ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው።


ባለሟሎቹንም ጠርቶ “ንጉሡ በአንተ ተደስቶአል፤ የእርሱ ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖቹም ይወዱሃል፤ ስለዚህ የእርሱን ልጅ ታገባ ዘንድ አሁን ጥሩ ጊዜ ገጥሞሃል” ብለው ለዳዊት በግል እንዲነግሩት አዘዘ።


ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች