Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እርሱ ግን ሊያዳምጣት አልፈቀደም፤ እርሱም ከእርስዋ ይልቅ ብርቱ ስለ ነበረ በኀይል አስገድዶ ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱ ግን ሊሰማት አልፈለገም፤ ከርሷ ይልቅ ብርቱ ስለ ነበር፣ በግድ አስነወራት፤ ከርሷም ጋራ ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እርሱ ግን ሊሰማት አልፈለገም፤ ከእርሷ ይልቅ ብርቱ ስለ ነበር፥ በግድ አስገድዶ ደፈራት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አም​ኖ​ንም ቃል​ዋን አል​ሰ​ማም፤ ይዞም አደ​ከ​ማት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ቃልዋን ግን አልሰማም፥ ከእርስዋ ይልቅ ብርቱ ነበረና በግድ አስነወራት፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:14
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአገሩ ገዢ የሒዋዊው የሐሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት፤ በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።


ከቤተሰብህ አንዱ ተነሥቶ ችግር እንዲያደርስብህ የማደርግ መሆኔን በመሐላ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው በምሰጥበት ጊዜ ይህ ነገር እንደሚፈጸም ትገነዘባለህ፤ እርሱም ከሚስቶችህ ጋር በቀን ብርሃን ይገናኛል።


ከዚያም በኋላ አምኖን እጅግ አድርጎ ጠላት፤ እንዲያውም ቀድሞ ካፈቀራት ይበልጥ አሁን በእርስዋ ላይ ያለው ጥላቻ ስለ ባሰ “ከዚህ ውጪልኝ!” አላት።


ምሕረትም ለመለመን አስቦ ንግሥት አስቴር በተቀመጠችበት ድንክ አልጋ ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ንጉሡም ከአትክልቱ ቦታ ተመልሶ ወደ ክፍሉ በገባ ጊዜ ይህን በማየቱ እጅግ ተቈጥቶ “ይህ ሰው በገዛ ቤተ መንግሥቴ ዐይኔ እያየ ንግሥቲቱን ሊደፍር ይፈልጋል እንዴ?” ሲል ጮኸበት። ንጉሡም ገና ይህን እንደ ተናገረ ወዲያውኑ ጃንደረቦቹ የሃማንን ፊት ሸፈኑ።


ከእኅትህ ጋር የፍትወተ ሥጋ ግንኙነት አታድርግ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የናትህ ልጅ፥ በቤት ወይም በውጪ የተወለደች ብትሆን ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።


“ ‘ከእኅቱ ወይም በአንድ በኩል ብቻ እኅቱ ከሆነች ሴት ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ አደጋ ለመጣል መጥተው በሌሊት ቤቱን ከበቡት፤ በመጀመሪያ እኔን ለመግደል አስበው ነበር፤ በኋላ ግን በቊባቴ ላይ ተረባርበው ስላመነዘሩባት ሞተች፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች