Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነርሱም ወደ ቤታቸው ለመመለስ አፈሩ፤ ዳዊት ስለ ሆነው ነገር በሰማ ጊዜ መልእክተኞች ልኮ በኢያሪኮ እንዲቈዩና ጺማቸውም እንደገና እስከሚያድግ እንዳይመለሱ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሰዎቹ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር መልክተኞቹን ላከባቸው፤ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪኮ ቈዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፥ ሰዎቹ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር መልክተኞቹን ላከባቸው፤ ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪ፥ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለዳ​ዊ​ትም ስለ ሰዎቹ ነገ​ሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍ​ረው ነበ​ሩና ተቀ​ባ​ዮ​ችን ላከ። ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ያን በሰማ ጊዜ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበሩና ተቀባዮች ላከ። ንጉሡም፦ ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 10:5
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ በአንድ በኩል ጺማቸውን ላጨ፤ ልብሳቸውንም በመቊረጥ እስከ ወገባቸው አሳጥሮ አባረራቸው፤


ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤


በአክዓብ ዘመነ መንግሥት ሒኤል ተብሎ የሚጠራ የቤትኤል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ሒኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ የበኲር ልጁ አቢራም ሞተበት፤ የቅጽርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ።


እነርሱም ወደ ቤታቸው ለመመለስ አፈሩ፤ ዳዊት ስለ ሆነው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ መልእክተኞች ልኮ በኢያሪኮ እንዲቈዩና ጢማቸው እስከሚያድግ ድረስ እንዳይመለሱ ነገራቸው።


እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ የኢያሪኮ ቅጽር በሮች ተዘግተው ነበር፤ ወደ ከተማይቱ መግባትም ሆነ መውጣት የሚችል ማንም አልነበረም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች