Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢዮአብም አቢሳይን እንዲህ አለው “ሶርያውያን ድል ሊያደርጉኝ መቃረባቸውን በምታይበት ጊዜ መጥተህ እርዳኝ፤ እኔም ዐሞናውያን አንተን ድል ሊያደርጉህ በሚቃረቡበት ጊዜ መጥቼ እረዳሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኢዮአብም እንዲህ አለ “ሶርያውያን የሚያይሉብኝ ከሆነ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን የሚያይሉብህ ከሆነ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም አለው፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ቢበ​ረ​ቱ​ብኝ ትረ​ዳ​ኛ​ለህ፤ የአ​ሞን ልጆ​ችም ቢበ​ረ​ቱ​ብህ እኔ መጥቼ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሶርያውያን ቢበረቱብኝ ትረዳኛለህ፥ የአሞን ልጆች ቢበረቱብህ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 10:11
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእናንተ እያንዳንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህ ዐይነት የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


እኛ በእምነት ብርቱዎች የሆንን፥ የደካሞችን ድካም መሸከም ይገባናል እንጂ ራሳችንን ብቻ የምናስደስት መሆን የለብንም፤


ነገር ግን የአንተ እምነት እንዳይጠፋ እኔ ለአንተ እጸልያለሁ፤ እንደገና በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና።”


የእምቢልታ ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ወደ እኔ መጥታችሁ በዙሪያዬ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋልናል” አልኳቸው፤


ከሠራዊቱ ቀሪውን ክፍል በወንድሙ በአቢሳይ ትእዛዝ ሥር አደረገ፤ አቢሳይም እነርሱን በዐሞናውያን ፊት ለፊት አሰለፋቸው፤


እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች