Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 8:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህም በኋላ አዛሄል ተመልሶ ሲመጣ “ኤልሳዕ ምን አለህ?” ሲል ቤንሀዳድ ጠየቀው። አዛሄልም “አንተ በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም አዛሄል ከኤልሳዕ ዘንድ ወጥቶ ወደ ጌታው ተመለሰ፤ ቤን ሃዳድም፣ “ለመሆኑ ኤልሳዕ ምን አለህ?” ሲል ጠየቀው፤ አዛሄልም፣ “በርግጥ ከበሽታህ እንደምትድን ነግሮኛል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚህም በኋላ አዛሄል ተመልሶ ሲመጣ “ኤልሳዕ ምን አለህ?” ሲል ቤንሀዳድ ጠየቀው። አዛሄልም “አንተ በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከኤ​ል​ሳ​ዕም ወጥቶ ወደ ጌታው መጣ፤ እር​ሱም፥ “ኤል​ሳዕ ምን አለህ?” አለው፤ እር​ሱም አለው፥ “መዳ​ንን ትድ​ና​ለህ በለው አለኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከኤልሳዕም ርቆ ወደ ጌታው መጣ፤ እርሱም “ኤልሳዕ ምን አለህ?” አለው። እርሱም “እንድትፈወስ ነገረኝ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 8:14
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ቤት ተመልሶ ገባ፤ ኤልሳዕም “እስከ አሁን የት ነበርክ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “ጌታዬ፥ ኧረ እኔ የትም አልሄድኩም” ሲል መለሰ።


ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤


ነገር ግን በማግስቱ አዛሄል ብርድልብስ ወስዶ ውሃ ውስጥ ነከረ፤ በዚያም ንጉሡን አፍኖ ገደለው። አዛሄልም በቤንሀዳድ እግር ተተክቶ የሶርያ ንጉሥ ሆነ።


እርሱም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች