Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 16:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የረማልያ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የረማልያ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ አካዝ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአታም ልጅ አካዝ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 16:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮአታም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ።


አካዝ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤


አካዝ፥ ሕዝቅያስ፥ ምናሴ፥


ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ የይሁዳ ነገሥታት ሆነው በነገሡባቸው ዘመናት የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፦


ከዖዝያን ልጅ ከኢዮአታም የተወለደው አካዝ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን፥ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የረማልያ ልጅ ፋቁሔ ጦርነት ማስነሣት ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌምን ድል ሊያደርጉአት አልቻሉም።


እግዚአብሔር እንደገና አካዝን እንዲህ አለው፦


እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “አንተና ልጅህ ሼርያሹብ ንጉሥ አካዝን ለመገናኘት ውጡ፤ እርሱንም ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚመጣበት በልብስ አጣቢዎች ቦታ ታገኙታላችሁ።


ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በይሁዳ ተከታትለው በነገሡባቸው ዘመናት፤ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው።


ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በተከታታይ በይሁዳ በነገሡበት ዘመን እግዚአብሔር ለሞሬታዊው ለሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ በገለጠለት ጊዜ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች