Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ሕዝብ፦ “በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ ባዕዳን አማልክትንና ዐስታሮትን ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ እግዚአብሔርም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፣ “በፍጹም ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ፣ ሌሎችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በፍጹም ልባችሁ ወደ ጌታ የምትመለሱ ከሆነ፥ ባዕዳን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለጌታ አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልኩ፤ እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ና​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፦ በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 7:3
40 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ንጹሕ ልብስም ልበሱ፤


ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።


ማርከው በወሰዱአቸው በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸው በእውነትና በቅን መንፈስ ተጸጽተው ንስሓ በመግባት አንተ ለቀድሞ አባቶቻችን ወደ ሰጠሃቸው ወደዚህች ምድር፥ አንተም ወደ መረጥኻት ወደዚህች ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፥


እኔን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፍሩ፤ እኔም ከጠላቶቻችሁ እጅ በመታደግ አድናችኋለሁ።”


እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤል አሠርቶት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ኢዮስያስ አፈራርሶ ጣለ፤ መሠዊያውን ነቅሎ፥ የተሠራበትን ድንጋይ ሁሉ ሰባብሮ በማድቀቅ እንደ ትቢያ አደረገው፤ የአሼራንም ምስል በእሳት አቃጠለ፤


እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”


ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤


ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”


ነገር ግን በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙትን የማምለኪያ ቦታዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም ወደ ቀድሞ አባቶቹ አምላክ ወደ እግዚአብሔር በሙሉ ልቡ ገና አልተመለሰም ነበር።


“የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በሥርዓት ያላነጹ ቢሆኑም እንኳ እነሆ በፍጹም ልባቸው አንተን በማምለክ ላይ ይገኛሉ፤ ስለዚህ በቸርነትህ ይቅር በላቸው!” ሲል ጸለየ፤


ሰው ዕቅድ ያወጣል፥ ነገር ግን ዕቅዱ በሥራ ላይ የሚውለው እግዚአብሔር ይሁን ብሎ ሲፈቅድ ብቻ ነው።


ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።


እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ። ከዚያ በኋላም በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ፥ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።


የይሁዳ ሕዝብ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት በሚሰሙበት ጊዜ ምናልባት ከክፉ ሥራቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ለመመለስ ከፈለጋችሁ እነዚያን አጸያፊ ጣዖቶችን አስወግዳችሁ ለእኔ ብቻ ታማኞች ብትሆኑ፥


“ስለዚህ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጣዖቶቻችሁን ትታችሁ ንስሓ ግቡ! ከአጸያፊ ተግባራችሁም ሁሉ ተመለሱ!’


ከክፉ ሥራችሁ ሁሉ ተላቃችሁ አዲስ መንፈስና አዲስ ልብ ይኑራችሁ፤ እናንተ እስራኤላውያን ለምን ትሞታላችሁ?


የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በኃጢአታችሁ ምክንያት የተሰናከላችሁ ስለ ሆነ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።


‘ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤


የዚያን ጊዜ ኢየሱስ “ ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ!’ ተብሎ ተጽፎአልና ወግድ አንተ ሰይጣን!” አለው።


“አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፤ ወይም አንዱን ይጠላል፥ ሌላውንም ይወዳል፤ ወይም አንዱን ያከብራል፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ አገልጋይ መሆን አይችልም።


ኢየሱስም፦ “ለጌታ ለአምላክህ ብቻ ስገድ! እርሱንም ብቻ አምልክ! ተብሎ ተጽፎአል፤” ሲል መለሰለት።


እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባቸዋል።”


አምላክህን እግዚአብሔርን በመፍራት ለእርሱ ታዘዝ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ፤ ለእርሱ ታማኝ ሆነህ በእርሱ ስም ብቻ ማል።


አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉት፤ እርሱን ብቻ ፍሩ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ቃሉንም ስሙ፤ እርሱንም አምልኩ፤ ከእርሱም ጋር ያላችሁ አንድነት የጠበቀ ይሁን።


በዚያም ስትኖሩ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትናፍቃላችሁ፤ እርሱንም በሙሉ ልባችሁ ብትሹት ታገኙታላችሁ፤


አምላክህን እግዚአብሔርን በመፍራት አክብረው፤ እርሱን ብቻ አምልክ፤ መሐላህም በእርሱ ስም ብቻ ይሁን።


እንዲሁም የገለዓድ እኩሌታ፥ አስታሮት እና ኤድራይ እነርሱም በባሳን የንጉሥ ዖግ ከተሞች የነበሩት ይህም ከምናሴ ነገድ ለእኩሌቶቹ የማኪር ልጆች እንደየወገናቸው ተከፋፈሉት።


ኢያሱ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አክብሩት፤ በፍጹም ቅንነትና በታማኝነት አገልግሉት፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶና በግብጽ ይሰግዱላቸው የነበሩትን ባዕዳን አማልክት አስወግዳችሁ እግዚአብሔርን ብቻ አምልኩ፤


እርሱም “እንግዲያውስ በመካከላችሁ የሚገኙትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አድርጉ” አላቸው።


ባዕዳን አማልክታቸውንም አስወግደው፥ እግዚአብሔርን አመለኩ፤ እግዚአብሔርም ስለ እስራኤል መከራ እጅግ አዘነ።


እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ሥራ በመሥራት እግዚአብሔርን በደሉ። በዓሊም ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤


እግዚአብሔርን ማምለክ ትተው “ባዓልና ዐስታሮት” ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤


ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የሳኦልን የጦር መሣሪያዎች ዐስታሮት ተብላ በምትጠራው ሴት አምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩ። የሳኦልንም ሬሳ ቤትሻን ተብላ በምትጠራው ከተማ ቅጽር ግንብ ላይ በምስማር ቸነከሩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች