Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ አወርዳለሁ፥ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 3:12
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን እንደ መዘዝኩና መልሼም ወደ አፎቱ እንደማልከተው ሰው ሁሉ ያውቃል።’


ነገር ግን አገልጋዮቼ በሆኑት በነቢያት አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁ ያስተላለፍኩትን ሕግና ትእዛዝ ባለመጠበቃቸው ተቀጥተው የለምን? ስለዚህ በበደላቸው ተጸጸተው ‘የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ባቀደው መሠረት እንደ ሥራችንና እንደ አካሄዳችን በእኛ ላይ ቅጣትን ማምጣቱ ትክክለኛ ነው’ አሉ።”


እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”


አምላካችሁ እግዚአብሔር የተናገረውን መልካም ነገር ሁሉ እንደ ፈጸመላችሁ፥ እንዲሁም እርሱ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስኪያጠፋችሁ ድረስ ክፉን ነገር ሁሉ ሊያመጣባችሁ ይችላል።


እነርሱም እርሱን ፈጽመው እስከሚያጠፉ ድረስ የእስራኤል ሕዝብ በያቢን ላይ እየበረቱ ሄዱ።


የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ተማረከ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ።


ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።


እርስዋም በእግዚአብሔር ታቦት መማረክ፥ በዐማትዋና በባልዋ መሞት ምክንያት ክብር ከእስራኤል ተለየ ስትል ልጅዋን ኢካቦድ ብላ ሰየመችው።


ቀጥላም “የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በመማረኩ ምክንያት የእግዚአብሔር ክብር ከእስራኤል ተለየ” አለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች