Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእ​ይም አይ​ገ​ለ​ጥም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፥ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፥ ራእይም አይገለጥም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 3:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእንግዲህ ወዲህ ተአምራት አይኖሩም፤ ነቢያትም አይኖሩም፤ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ እንደሚቈይ ከእኛ መካከል ማን ያውቃል?


ከእግዚአብሔር የሚገለጥ መመሪያ ባይኖር ሕዝብ መረን ይለቀቃል፤ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያከብር ሰው ግን የተባረከ ነው።


ሰውን ከወርቅ ይልቅ፥ ከኦፌር ወርቅም የበለጠ ብርቅና ውድ አደርገዋለሁ።


አንዱ መቅሠፍት ሌላውን ያስከትላል፤ አንዱ ወሬም ሌላውን ወሬ ተከታትሎ ይመጣል፤ ነቢያት ያዩትን ራእይ እንዲነግሩአችሁ ትለምኑአቸዋላችሁ፤ ካህናት ሕዝቡን የሚያስተምሩት ሕግ፥ ሽማግሌዎችም ለሕዝቡ የሚሰጡት ምክር ጠፋባቸው።


ከዚህ በኋላ ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ ሕፃኑ ሳሙኤልም በካህኑ ዔሊ ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።


ሳሙኤል ግን ገና በልጅነቱ ከበፍታ የተሠራ ሸሚዝ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር፤ ይህም ቃል በዕብራይስጡ ካህኑ ለሚለብሰው ልብስ ወይም በደረቱ ላይ ስለሚያደርገው ነገር መጠሪያ ነው።


ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።


ከአንተ ዘሮች መካከል በሕይወት የሚተርፍ ሁሉ ወደዚያ ካህን ዘንድ እየሄደ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ከእርሱ ገንዘብና ምግብ ይለምናል፤ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘትም ሲል ካህናትን በረዳትነት ማገልገል እንዲፈቀድለት ይለምናል።’ ”


ሳሙኤልም እስኪነጋ ድረስ ተኝቶ ቈየ፤ በነጋም ጊዜ ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ያየውንም ራእይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ፤


እግዚአብሔርም በሴሎ መገለጡን ቀጠለ፤ እዚያም በቃሉ ለሳሙኤል ተገለጠለት። የሳሙኤልም ቃል በመላው እስራኤል ተደማጭነትን አገኘ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች