Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ንጉሡም “አይዞሽ አትፍሪ! ይልቅስ የምታዪው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እኔ አንድ መለኮታዊ ግርማ ያለው ከመቃብር ሲወጣ እያየሁ ነኝ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ንጉሡም፣ “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትዮዋም፣ “መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ንጉሡም፥ “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትዮዋም፥ “አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ንጉ​ሡም፥ “አት​ፍሪ ፤ ንገ​ሪኝ፤ ማንን አየሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “አማ​ል​ክት ከም​ድር ሲወጡ አየሁ” አለ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ንጉሡም፦ አትፍሪ፥ ያየሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፦ አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:13
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አትናገር፤ የሕዝብህንም መሪ አትስደብ።


እርሱ አንተን ወክሎ ይናገራል፤ በአንተም ስም ቃሉን ለሕዝቡ ያስተላልፋል፤ አንተም ለእርሱ እንደ አምላክ ትሆናለህ።


እርስዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ በመጮኽ “ስለምን አታለልከኝ? አንተ ንጉሥ ሳኦል ነህ!” አለችው።


እርሱም “መልኩ ምንን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እነሆ፥ ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየተነሣ ነው” ስትል መለሰችለት። ሳኦልም ያ ሳሙኤል መሆኑን ዐውቆ ስለ ክብሩ በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች