Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 26:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚያም በፍጥነት ተነሥቶ በመሄድ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የሚተኙበትን ቦታ አረጋገጠ፤ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ ወታደሮቹ በዙሪያው ይገኙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አለቃ፣ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ፣ ሰራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ፥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሠራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ፥ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም በቀ​ስታ ተነ​ሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈ​ረ​በት ቦታ መጣ፤ ሳኦ​ልና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርም የተ​ኙ​በ​ትን ስፍራ አየ፤ ሳኦ​ልም በድ​ን​ኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ሰፍሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፥ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አበኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፥ ሳኦልም በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 26:5
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።


ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ንጉሥ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታን፥ ማልኪሹዓ፥ አቢናዳብና ኤሽባዓል ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ፤


ዳዊትም በማግስቱ ማልዶ ተነሣ፤ በጎቹን ለሌላ እረኛ በመተው እሴይ ባዘዘው መሠረት የተዘጋጀውን ምግብ ይዞ ሄደ፤ እስራኤላውያን ጦርነት ለመግጠም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሚደነፉበት ጊዜ ዳዊት ወደ ጦሩ ሰፈር ደረሰ።


ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።


መልእክተኞች ልኮ በማሰለል ሳኦል በእርግጥ እዚያ መድረሱን ዐወቀ፤


ከብንያም ነገድ ቂስ ተብሎ የሚጠራ ታዋቂነት ያለው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጸሮር የልጅ ልጅ ሲሆን ከአፊሐ ጐሣ ወገን የበኮራት ቤተሰብ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች