Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 22:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ነገር ግን አብያታር የሚባል ከአቤሜሌክ ወንዶች ልጆች አንዱ ብቻ አምልጦ በመሄድ ከዳዊት ጋር ተቀላቀለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የአኪጦብ ልጅ፣ የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ግን አምልጦ ዳዊት ወዳለበት ሸሸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የአኪጦብ ልጅ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ግን አምልጦ ዳዊት ወዳለበት ሸሸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጆች ስሙ አብ​ያ​ታር የሚ​ባል አንዱ ልጅ አም​ልጦ ሸሸ፤ ዳዊ​ት​ንም ተከ​ተለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከአኪጦብም ልጅ ከአቢሜሌክ ልጆች ስሙ አብያታር የሚባል አንዱ ልጅ አምልጦ ወደ ዳዊት ሸሸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 22:20
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአቤሜሌክ ልጅ አብያታር አምልጦ በቀዒላ ከዳዊት ጋር በተባበረ ጊዜ ወደዚያ የመጣው ኤፉዱን እንደ ያዘ ነበር።


ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን አመጣለት፤


ዳዊትም ሳኦል አደጋ ሊጥልበት ማቀዱን በሰማ ጊዜ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን ይዘህ ና!” አለው።


ከበረሓ የተነሣ ዐውሎ ነፋስ በድንገት መጥቶ ቤቱን በሙሉ በገለባበጠው ጊዜ ቤቱ በላያቸው ላይ ስለ ተደረመሰ ሞቱ፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።


ነገዱ ከብንያም ወገን የሆነ አንድ ሰው ከጦር ሜዳ ተነሥቶ በመገሥገሥ በዚያኑ ዕለት ሴሎ ደረሰ፤ ሐዘኑንም ለማሳወቅ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤


በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በወጣትነት ዕድሜአቸው በሰይፍ ያልቃሉ፤


ሱሳ የቤተ መንግሥት ጸሐፊ ሲሆን፥ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤


በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ ካህኑ ፊንሐስ የወለደው የኢካቦድ ወንድም የአሒጡብ ልጅ አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእርሱ ጋር አብሮ ነበር። እነርሱም ዮናታን ወዴት እንደ ሄደ አላወቁም ነበር።


ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንዴት እንደ ፈጀም ለዳዊት ነገረው፤


ካህኑ ሳዶቅም እዚያው ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሌዋውያን ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት፥ ሕዝቡ ሁሉ ከተማውን ለቆ እስኪወጣ ድረስ በአብያታር አጠገብ አስቀመጡት።


ስለዚህም ጉዳይ ከጸሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም ዓላማውን ደገፉ፤


ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲሁም ኡሪኤልን፥ ዐሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሸማዕያን፥ ኤሊኤልንና ዓሚናዳብን በአጠቃላይ ስድስት ሌዋውያንን ወደ ድንኳን ውስጥ አስገባ።


የአሒጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቤሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሱሳ የቤተ መንግሥት ጸሐፊ ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች