Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሳኦልም ዮናታን የተናገረውን ቃል በመስማት ዳዊትን እንደማይገድለው የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ በመማል አረጋገጠ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሳኦልም ዮናታንን ካዳመጠው በኋላ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም” ብሎ ማለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሳኦልም ዮናታንን ካዳመጠው በኋላ፥ “በሕያው ጌታ እምላለሁ! ዳዊት አይገደልም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሳኦልም የዮናታንን ቃል ሰማ፥ ሳኦልም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም ብሎ ማለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:6
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንተ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ በስሜ ትምላላችሁ፤ ነገር ግን የምትምሉት በሐሰት ነው።”


ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥ ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥ ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥


ከዚያም በኋላ ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዐይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” አላት።


በደል ሠርቶ የተገኘው ሰው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን በሞት እንደሚቀጣ ለእስራኤል ድልን በሰጠው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።” ነገር ግን አንዳች መልስ የሰጠው ሰው አልተገኘም።


እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”


ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ ይህን ሁሉ ከነገረው በኋላ ወደ ሳኦል አቀረበው፤ ዳዊትም ከዚያ በፊት ያደርገው እንደ ነበር በንጉሡ ፊት እንደ ቀድሞው ማገልገሉን ቀጠለ።


“ልጄ ሆይ! ስለ ራሳቸው ችግር መናገር ለማይችሉ ሰዎች አንተ ተናገርላቸው፤ ፍርድ አጥተው ለተጨነቁ ሰዎች መብታቸውን አስከብርላቸው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች