Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን የገደለው በገዛ ሕይወቱ ቈርጦ ነው። እግዚአብሔር ለመላው እስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም አይተህ ደስ አለህ። ታዲያ እርሱን በከንቱ በመግደል ዳዊትን በመሰለ ንጹሕ ሰው ላይ ለምን በደል ትፈጽማለህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን የገደለው በገዛ ሕይወቱ ቆርጦ ነው። ጌታ ለመላው እስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም አይተህ ደስ አለህ። ታዲያ እርሱን በከንቱ በመግደል ዳዊትን በመሰለ ንጹሕ ሰው ላይ ለምን በደል ትፈጽማለህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊውን ገደለ፥ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ሁሉ ታላቅ መድኃኒት አደረገ፥ አንተም አይተህ ደስ አለህ፥ በከንቱ ዳዊትን በመግደልህ ስለ ምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ? ብሎ ስለ ዳዊት መልካም ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:5
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱና ተከታዮቹ በዚያው በማሳው ውስጥ ፍልስጥኤማውያንን ተቋቊመው ወጉአቸው፤ እግዚአብሔርም ታላቅ ድልን አጐናጸፋቸው።


ሳኦል ግን “በዛሬው ቀን እግዚአብሔር እስራኤልን ስላዳነ ማንም ሰው መገደል የለበትም” አለ።


“ንጹሑን ሰው ለሞት አሳልፌ በመስጠቴ በድዬአለሁ።” እነርሱ ግን “ታዲያ፥ እኛ ምን ቸገረን! የራስህ ጉዳይ ነው!” አሉት።


ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ።


አባቴ ለእናንተ እንደ ተዋጋና እናንተንም ከምድያማውያን እጅ ለማዳን ሲል ሕይወቱን በአደጋ ላይ ጥሎ እንደ ነበረ አስታውሱ፤


የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።


ሕይወቴ በአደጋ ላይ ቢሆንም እንኳ ሕግህን አልረሳም


ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤


እናንተ በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን ርዳታ እርሱ ለማሟላት ብሎ ስለ ክርስቶስ ሥራ ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለሞት ተቃርቦ ነበር።


ይህም የሆነው፥ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።


ስለዚህ ጲላጦስ ይህ ነገር ሁከት እንደሚያስነሣ እንጂ ሌላ ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ ውሃ አስመጥቶ “እኔ ለዚህ ሰው ሞት ኀላፊ አይደለሁም፤ ኀላፊነቱ የእናንተ ነው!” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።


ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።”


ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጒር ይልቅ በዝተዋል፤ ብዙዎች ጠላቶቼ ሊያጠፉኝ ይፈልጋሉ ያልሰረቅኹትን ነገር መመለስ አለብኝን?


ሕዝቡ ግን ሳኦልን “ይህን ታላቅ ድል ለእስራኤል ያስገኘ ዮናታን ይሞታልን? ከቶ አይደረግም! መሞቱ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ አንዲቱ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም እንምላለን፤ ዛሬ እርሱ ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ረዳትነት የተፈጸመ ነው” አሉ፤ በዚህም ዐይነት ሕዝቡ ዮናታንን ከሞት ቅጣት አዳኑት።


እናንተ እኔን ለመርዳት አለመፈለጋችሁን ባየሁ ጊዜ ለሕይወቴ ሳልሳሳ እነርሱን ለመውጋት ወሰኑን ተሻግሬ ሄድሁ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኝ። ታዲያ፥ አሁን እኔን ለመውጋት የተነሣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?”


ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ! ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን የሚያደርገውን ዛሬ ታያላችሁ፤ እነዚህን ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም።


በአንተ የሚታመኑት ኀፍረት አይደርስባቸውም፤ ኀፍረት የሚደርስባቸው፥ በአንተ ላይ ለማመፅ የሚጣደፉት ናቸው።


ሳኦልም ዮናታን የተናገረውን ቃል በመስማት ዳዊትን እንደማይገድለው የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ በመማል አረጋገጠ፤


አቤሜሌክም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ዳዊት ለአንተ የታመነ የጦር መኰንን ነው፤ የአንተው የራስህ ዐማች ከመሆኑም ሌላ የክብር ዘብህ አዛዥ ነው፤ በቤተ መንግሥትህም አደባባይ እንደ እርሱ የሚከበር ማን አለ?


ይህ ሰው ግን ባለበት ጸንቶ በመቆም እጁ ዝሎ በሰይፉ ላይ እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር ታላቅ ድልን አደረገ፤ ጦርነቱም ከቆመ በኋላ እስራኤላውያን አልዓዛር ወደነበረበት ስፍራ ተመልሰው ከሞቱት ፍልስጥኤማውያን ብዙ የጦር ልብስ ማረኩ።


እነርሱ በደጋግ ሰዎች ላይ ያሤራሉ፤ በንጹሓን ሰዎች ላይም የሞት ፍርድ ይበይናሉ።


በዚህን ጊዜ ሦስቱ ዝነኛ ወታደሮች የፍልስጥኤማውያንን ሰፈር ጥሰው በማለፍ ከጒድጓዱ ውሃ ቀዱና ለዳዊት ይዘውለት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጠጣው አልወደደም፤ በዚህ ፈንታ ለእግዚአብሔር እንደ መባ አድርጎ አፈሰሰው።


በመልካም ፈንታ ክፉ፥ በፍቅር ፈንታ ጥላቻ ይመልሱልኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች