Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዳዊትም የያዘውን ምግብ ለስንቅ ጠባቂው ትቶ ወደ ጦሩ ግንባር እየሮጠ ወደ ወንድሞቹ ሄደ፤ ስለ ደኅንነታቸውም ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳዊትም ዕቃውን በዕቃ ጠባቂው እጅ አኖረው፥ ወደ ሠራዊቱም ሮጠ፥ የወንድሞቹንም ደኅንነት ጠየቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:22
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጠላት ሠራዊት ወደ ዓይ ከተማ ደረሰ፤ በሚግሮንም በኩል ሲያልፉ ጓዛቸውን በሚክማስ አኖሩ።


ወጣቱ ሌዋዊ ወደሚኖርበትም ወደ ሚካ ቤት ገቡ፤ ሌዋዊውንም እንዴት እንደሚኖር ጠየቁት፤


አባቱም “በል እንግዲህ ሂድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዐይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም ደረሰ።


እነርሱም ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ከፊት አስቀድመው ወደ ኋላ በመመለስ ጒዞአቸውን ቀጠሉ።


የፍልስጥኤማውያን ሠራዊትና የእስራኤላውያን ሠራዊት ቦታ ቦታቸውን ይዘው በጦሩ ግንባር ፊት ለፊት በመተያየት ላይ ነበሩ።


ኦርዮ በደረሰ ጊዜ ዳዊት “ኢዮአብና ሠራዊቱ ሁሉ እንዴት ናቸው? የጦርነቱስ ሁኔታ እንዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤


ስለዚህም ሙሴ ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ እጅ በመንሣት ሳመው፤ ስለ ግል ጤንነታቸው ተጠያይቀው ወደ ሙሴ ድንኳን ገቡ፤


ስለዚህም ዐሥር መልእክተኞችን መርጦ ወደ ቀርሜሎስ እንዲሄዱና ናባልን አግኝተው የእርሱን ሰላምታ እንዲያቀርቡለት አዘዛቸው፤


ዳዊትም ደክሞአቸው በብሦር ምንጭ አጠገብ ዕረፍት በማድረግ ቈይተው ወደነበሩት ወደ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ተመልሶ ሄደ። እነርሱም ዳዊትንና ተከታዮቹን ሊቀበሉአቸው መጡ፤ ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ ደኅንነታቸውን በመጠየቅ ሰላምታ አቀረበላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች