Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሳኦል ወደ ጊብዓ በደረሰ ጊዜ የነቢያት ጉባኤ ከሳኦል ጋር ተገናኘ፤ በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ላይ ወረደ፤ በዚያን ጊዜም እርሱ ከእነርሱ ጋር ትንቢት መናገር ጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጊብዓ በደረሱ ጊዜ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋራ ትንቢት ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጊብዓ በደረሱ ጊዜ፥ እነሆ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ወደ​ዚ​ያም ኮረ​ብታ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነ​ቢ​ያት ጉባኤ አገ​ኙት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 10:10
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።


ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኀይል ወረደ፤ የሳኦልም ቊጣ እጅግ ገነፈለ።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው።


ሶምሶንም ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እየደነፉ መጡበት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አበረታው፤ ክንዱ የታሰሩበት ገመዶች እሳት እንደ ነካቸው የሐር ፈትል ከእጁ ላይ ቀልጠው ወደቁ።


ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች