Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሶፎንያስ 3:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በዚያ ዘመን እሰበስባችኋለሁ፥ በሰበሰብኳችሁም ጊዜ፤ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በዚያ ጊዜ እሰበስባችኋለሁ፤ ያን ጊዜ ወደ አገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ ዐይናችሁ እያየ፣ ምርኳችሁን በምመልስበት ጊዜ፣ መከበርንና መወደስን፣ በምድር ሕዝብ ሁሉ መካከል እሰጣችኋለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ሰብስቤ ወደ ሀገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ ንብረታችሁን ሁሉ ዐይናችሁ እያየ በምመልስላችሁ ጊዜ በምድር ሕዝቦች ሁሉ ፊት ዝነኞችና የተመሰገናችሁ ትሆናላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፥ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሶፎንያስ 3:20
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእናንተም ዘንድ ታገኙኛላችሁ፥ ይላል ጌታ፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እናንተንም ለምርኮ ካፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።


ሕዝቦች ሁሉ የተባረኩ ብለው ይጠሩአችኋል፥ የደስታ ምድር ትሆናላችሁና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ሁሉ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ።


እነሆ በዚያ ዘመን፥ ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፤ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ።


የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ዳግም ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ የአትክልት ስፍራዎችንም ያበጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።


እነሆም፥ በዚያ ወራትና በዚያ ዘመን፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥


የጠፋውን እፈልጋለሁ፥ የባዘነውን እመልሳለሁ፥ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን አጠፋለሁ፤ በፍትሕም እጠብቀዋለሁ።


ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።


የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፤ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ፤ ጌታ አምላካቸው ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳል።


እኔ ጌታ አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ፥ በአሕዛብ እንዲማረኩ አድርጌአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና፥ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ በዚያ አላስቀርም።


አንተም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ሕዝቦች መካከል እወስዳለሁ፥ ከየስፍራውም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ በሰበሰብሁ ጊዜ፥ በአሕዛብም ፊት በተቀደስሁባቸው ጊዜ፥ ለባርያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድራቸው ይቀመጣሉ።


እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ።


ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ ጌታ የባረከው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል።


መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ይሁን፥ የጌታም መልአክ ያሳድዳቸው።


ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ መቃብራችሁን እከፍታለሁ፥ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣችኋለሁ።


“ጌታ የተቤዣቸው፥ የተቀደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፥ “የተፈለገች፥ ያልተተወችም ከተማ” ትባያለሽ።


ምርኮአቸውን እመልሳለሁ፤ የሰዶምና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ የሰማርያንና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ በመካከላቸው ያለውን የአንቺንም ምርኮ እመልሳለሁ፥


ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ለእርሱም ዕረፍት አትስጡት።


ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፦ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ ይላል።


ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፥ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ ዛሬ ተናግሮአል፤


ከፈጠራቸውም አሕዛብ ሁሉ በምስጋናና በስም፥ በክብር ከፍ እንደሚያደርግህና እርሱም እንደ ተናገረ ለጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ አደረገህ።”


እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል ጌታ፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይወርሱአታል፥ ይላል ጌታ።”


የምድሪቱ ሕዝቦች ሁሉ ይቀብሩአቸዋል፤ በምከበርበት ቀን፥ ለሥም ይሆንላቸዋል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲኖሩ አመጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በታማኝነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።


የመንጋዬንም ትሩፍ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ራሴ ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ፥ ይበዛሉም።


የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።


ያዕቆብ ሆይ፥ ሁላችሁንም ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልን ትሩፍ በአንድ ላይ እሰበስባለሁ፤ በጋጣ ውስጥ እንዳሉ በጎች፥ በማሰማርያው ውስጥ እንዳለ መንጋ አደርገዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።


አንካሳይቱን ትሩፍ፥ የተጣለችውን ብርቱ መንግሥት አደርጋታለሁ፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በጽዮን ተራራ ጌታ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።


የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ በረከት መሆን እንድትችሉ አድናችኋለሁ፤ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች