Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሶፎንያስ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታን ከመከተል የተመለሱትን፥ ጌታን ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣ እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከእኔ የራቁትን፥ እኔን መከተል የተዉትንና ወደ እኔም መጥተው እኔ እንድመራቸው ያልጠየቁኝን አጠፋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሶፎንያስ 1:6
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።


እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፤ በደል የሞላበት ወገን፤ የክፉ አድራጊ ዘር፤ ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ! ጌታን ትተዋል፤ የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ ጀርባቸውንም በእርሱ ላይ አዙረዋል።


አንቺ እኔን ትተሺኛል፥ ይላል ጌታ፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፤ ይቅርታን ከማድረግ ደክሜአለሁ።


በመንገድ በመራሽ ጊዜ ጌታ አምላክሽን በመተው በራስሽ ላይ ይህን አላመጣሽምን?


ሕዝቤም ከእኔ ወደ ኋላ መመለስን በጽኑ ወደዱ፤ በአንድነትም ወደ ልዑሉ ይጣራሉ፥ እርሱ ግን ከፍ ከፍ አያደርጋቸውም።


በዚህም ሁሉ ግን አታላይቱ ይሁዳ በሐሰት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም፥ ይላል ጌታ።


ስለዚህ ጌታ ራስንና ጅራትን፤ የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።


እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።


ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።


ክፉ በትዕቢቱ ጌታን አይፈልገውም፥ በሐሳቡ በሙሉ እግዚአብሔር የለም።


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፥ ፈራጆቻቸውንም አጥፍተዋል፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወድቀዋል፤ ከእነርሱም መካከል ወደ እኔ የጮኸ የለም።


እራሱን ሸንግሎአልና፥ ኃጢአቱን መቀበልና መጥላት ይሳነዋል።


የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤


ያዕቆብ ሆይ፥ አንተ ግን አልጠራኸኝም፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ደክመሃል።


ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።


የእስራኤልም ትዕቢት በራሱ ላይ መስክሮአል፤ ወደ አምላካቸው ወደ ጌታ ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።


እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ከእነርሱ እነርሱም ከእናንተ ጋር በጋብቻ ቢተሳሰሩ፥


የጌታን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ ከአምላኬ ክፋት በማድረግ አልተለየሁም።


የእስራኤልንም አምላክ ጌታን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ እንዲገደል ማሉ።


ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።


ማንንም አታዳምጥም፥ እርምት አትቀበልም፥ በጌታ አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች