ዘካርያስ 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አሁንም በዓይኔ ስቃያቸውን አይቻለሁና ከዚህ በኋላ ጨቋኝ አይመጣባቸውም፤ በቤቴ ዙሪያ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ ከዘራፊዎች የሚጠብቅ እንዲሰፍር አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ከዚህ በኋላ ምድሬን ዙሪያዋን ከብቤ እጠብቃለሁ፤ የወራሪ ኀይል መተላለፊያም አላደርጋትም። ሕዝቤ ምን ያኽል እንደ ተሠቃየ ስለ ተመለከትኩ ከእንግዲህ ወዲህ ጨቋኞች አይወሩአቸውም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እኔም ማንም እንዳይሄድና እንዳይመለስ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ በቤቴ ዙሪያ ሰፈር አደርጋለሁ፣ አሁንም በዓይኔ አይቻለሁና ከዚህ በኋላ አስጨናቂ አያልፍባቸውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እኔም ማንም እንዳይሄድና እንዳይመለስ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ በቤቴ ዙሪያ ሰፈር አደርጋለሁ፥ አሁንም በዓይኔ አይቻለሁና ከዚህ በኋላ አስጨናቂ አያልፍባቸውም። ምዕራፉን ተመልከት |