Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘካርያስ 8:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከፀምዕራብ ምድር እታደገዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቤን ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እኔ ሕዝቤን በስደት ከሚኖሩበት ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋቸዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘካርያስ 8:7
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።”


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የጌታ ስም ይመስገን።


ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።


የአሳፍ መዝሙር። የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።


ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ። እነሆ፥ እነዚህ ከሩቅ፥ እነሆም፥ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፥ እነዚህም ከሲኒም አገር ይመጣሉ።”


እርሱ የጌታ ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የጌታን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።


እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዓይነ ስውርና አንካሳው ያረገዘችና ምጥ የያዛትም በአንድነት ይሆናሉ፤ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፥ ከተበተናችሁባቸው አገሮችም እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከኃጢአታችሁ ሁሉ በማነጻችሁ ቀን በከተሞች ሰዎችን አኖራለሁ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ።


የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ ስለምራራላቸው ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው ጌታ ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁ።


“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።


ጌታ አምላክህ ምርኮህን ይመልስልሃል፤ ይራራልሃልም፤ አንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል ጌታ እግዚአብሔር እንደገና ይሰበስብሃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች