ዘካርያስ 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ከነዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰው ደሞዝ፥ ለእንስሳ ኪራይ አልነበረም፤ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ስለ ነበር፥ በጠላቶቻቸው የተነሣ ወደዚያ ለሚገቡትና ለሚወጡት ሰላም አልነበራቸውም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ከዚያ በፊት ለሰው ደመወዝ፣ ለእንስሳም ኪራይ አይከፈልም ነበር፤ ጠላት በመኖሩም ማንም ሥራውን በሰላም ማከናወን አልቻለም፤ እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው ላይ እንዲነሣ አድርጌ ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ከእነዚያ ቀኖች በፊት ለሰዎች የድካም ዋጋ ለእንስሶችም ኪራይ አይከፈልም ነበር፤ ሰውን ሁሉ በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣሣ ስላደረግሁ ማንም ሰው ሲወጣና ሲገባ ሰላም አልነበረውም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ከዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰውና ለእንስሳ ዋጋ አልነበረምና፣ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ነበርና ከአስጨናቂው የተነሣ ለሚገባውና ለሚወጣው ሰላም አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ከዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰውና ለእንስሳ ዋጋ አልነበረምና፥ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ነበርና ከአስጨናቂው የተነሣ ለሚገባውና ለሚወጣው ሰላም አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከት |